🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት የሚከታተል የሙያ ፈቃድ ካውንስል | STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት የሚከታተል የሙያ ፈቃድ ካውንስል ሊመሰረት ነው።
------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳትን የሚከታተል የሙያ ፍቃድ ካውንስል ለመመሰረት ውይይት እያካሄደ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሁሪያ ዓሊ ለመምህራንና ለትምህርት አመራሮች የሙያ ፍቃድ መስጠትና ማደስ መምህሩንና የትምህርት አመራሩን በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ተግተው እንዲሰሩ ያስችላል ብለዋል።

የሙያ ፍቃድ መስጠትና ማደስ ለትውልዱ ጥራት ያለው ትምህርት ተደራሽ እንዲሆን የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ሚኒስትር ዴኤታ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ በበኩላቸው የመምህራን ሙያ ፈቃድ አሰጣጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ስታንዳርድ ተቀምጦለት የሚከናወን እንደሆነና ውጤታማ የሆነ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል፡፡

በካውንስል ምስረታው ላይ የክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲኖች፣ የኢትዮጵያ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

#SHARE
መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ያጋሩ

ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT