Get Mystery Box with random crypto!

...... አለን...... ሁሌ በቀን በቀን ኑሮ እንዳሳቀቀን ስናገኝም ስቀን ስናጣም ተንቀን አለን | ✨şõmé thìnğ☔️

...... አለን......
ሁሌ በቀን በቀን
ኑሮ እንዳሳቀቀን
ስናገኝም ስቀን
ስናጣም ተንቀን
አለን...............
ትናንትናን ቆመን
ዛሬን አንቀላፍተን
ነገን ተጎልተን
መራመድን ፈርተን
የሂወት ጣዕሙ
የመኖር ትርጉሙ
አልገባ ስላለን
ለጠየቀን ሁሉ...አለን....አለንንን
እንላለን።

@never_minde
@never_minde