Get Mystery Box with random crypto!

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከምንም አይነት ስጋቶች ነፃ ነው-አዲሷ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥ | Nib InternationalBank

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከምንም አይነት ስጋቶች ነፃ ነው-አዲሷ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰ።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ዛሬ ከባንኩ ባለድርሻ አካላት ጋር የትውውቅ መድረክ አከናውነዋል።

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ ስለ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ለባለአክሲዮኖችና ደንበኞች ገለጻ አድርገዋል። ''ቦርዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለመምረጥ ባደረገው ምልመላ የአሁኗን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የመረጠ ሲሆን ሹመታቸው ፀድቆ በዚህ ወሳኝ ወቅት ዶክተር እመቤት ወደባንካችን በመምጣታቸው ደስተኞች ነን'' ብለዋል።

ቦርዱ በተለይም ከክፍያ ጋር ተያይዞ የነበሩ ውስንነቶችን መቅረፍ መቻሉን ያብራሩት ሊቀመንበሩ፤ አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት ያላቸውን እምቅ አቅም በመጠቀም ባለአክሲዮኖች በአጭር ጊዜ ባንኩን ወደነበረበትና ከዚያም በላይ የላቀ ደረጃ ለማድረስ በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

''ንብ ባንክ አሁን ላይ ምንም አይነት ስጋት የለበትም'' ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ''ወደ ንብ ባንክ በሃላፊነት እንደመጣሁ ባለአክስዮኖችን ጨምሮ ከባንኩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያደረግኩት ውይይት ችግሩ በአጭር ጊዜ የሚቀረፍ መሆኑን አመላክቶኛል'' ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም ባለአክሲዮኖች፣ ደንበኞችና ሌሎች የባንኩ ባለድርሻ አካላት ከጎናቸው እንዲቆሙ ጠይቀዋል። አስተያየት የሰጡ ባለአክሲዮኖች እና ደንበኞች በዋና ሥራ አስፈጻሚዋ መደሰታቸውን ገልፀው በዘርፉ የነበራቸውን ልምድ መነሻ በማድረግ ንብ ባንክን ወደተሻለ ስኬት እንደሚያሸጋግሩት ያላቸውን እምነትና ተሥፋ ገልፀዋል። ለዚህም ባንኩ በሚፈልጋቸው የትኛውም ወቅት ፈጣንና ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!