Get Mystery Box with random crypto!

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ። ባንኩን ከተቀላቀሉ አዳዲስ የማኔጅመንት አባላት | Nib InternationalBank

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ።

ባንኩን ከተቀላቀሉ አዳዲስ የማኔጅመንት አባላት ጋር የትውውቅ መድረክ ተካሄደ።

''በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጥቷል፡፡

በቅርቡ የተወሰኑ ቺፎች፣ ምክትል ቺፎች፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የመምሪያ ዳይሬክተሮች ከኃላፊነት መነሳታቸው ይታወሳል። በምትካቸውም አዳዲስ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሹመዋል፡፡

በዚህም መሠረት፦ አቶ ግርማ ፈቀደ - ቺፍ ደንበኞችና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ኦፊሰር፣ አቶ ሳምሶን አምዲሳ - ቺፍ ፋይናንስና ፋሲሊቲ ኦፊሰር፣ አቶ በላይ ጎርፉ - ምክትል ቺፍ ስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ኦፊሰር፣ ወይዘሮ ሐረገወይን አምሳለ - ምክትል ቺፍ ዓለም አቀፍ ባንኪንግ ኦፊሰር፣ አቶ ዘውዱ ሐኪሙ - ምክትል ቺፍ ሒዩማን ካፒታል ኦፊሰር እና አቶ ነጻነት ይርጋ ምክትል ቺፍ ክሬዲት ኦፊሰር በመሆን ተሹመዋል፡፡

በተያያዘም፣ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም አዳዲስ የሥራ ኃላፊዎች ከቀሪዎቹ ነባር የማኔጅመንት አባላት ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት የትውውቅ መድረክ አካሂደዋል፡፡

ባንኩን የተቀላቀሉት አዲሶቹ የማኔጅመንት አባላት፤ ቀድሞ ይሠሩበት ከነበረው ተቋም በተሻለ ደረጃ ለማገልገልና ባንኩ አሁን ካለበት ችግር እንዲላቀቅ በላቀ ትጋት ለማገልገል እንደተዘጋጁ አረጋግጠዋል፡፡ “ምቹና ከስጋት ነጻ ከሆነ ሥራ ላይ ወጥቶ ተግዳሮት ወዳለበት የሥራ ከባቢን መቀላቀል እጅግ ተፈላጊና መልካም አጋጣሚ ነው”ም ብለዋል፡፡
***
ይሰሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!