Get Mystery Box with random crypto!

Path

Logo of telegram channel onapath — Path P
Logo of telegram channel onapath — Path
Channel address: @onapath
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 336
Description from channel

"Art is not what you see, it's what you make others see."

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 2

2022-04-12 07:33:14
278 views04:33
Open / Comment
2022-04-11 01:21:23
320 views22:21
Open / Comment
2022-04-09 11:02:10
224 views08:02
Open / Comment
2022-04-07 07:34:09
213 views04:34
Open / Comment
2022-04-01 20:23:10 ጥቂት ጊዜ...
___

ሁለት የዜን መነኮሳት ወደ ገዳማቸው ለመድረስ በሚፋጠኑበት አንድ ማምሻ በመንገዳቸው የሚገኝን ወንዝ እየተሻገሩ ሳለ አንዲት ሴት የሚገማሸረው ወራጅ ውሃ ከወዲያ ወዲህ እያላጋት በጎርፉ ላለመወሰድ ሳሩንና አለቱን እየቧጠጠች ስትታገል ያዩዋታል... ሴቲቱ እጃቸውን ብትዋስ ልትድን የምትችል ቢሆንም የሴትን ገላ መንካት በሚከለክለው የዜን ሕግ ምክንያት አልፈዋት ሊሄዱ ሆነ...
___

በዚህ መሃል አንዱ መነኩሴ ከጉዞው ተናጠበና ወደ ወንዙ ዘልሎ ገባ... ሴቲቱንም ተሸክሞ በማውጣት ከወንዙ ዳር አድርሶ አስፈላጊውን እርዳታ አደረገላት... ሴቲቱ በአጸፋው ምስጋና አቀረበች... ባልንጀራው ዳር ቆሞ ሁኔታውን ይታዘባል...
___

ፀሐይ እየጠለቀች ነው... መነኩሴዎቹ ለሰርክ ምለላ ፈጥነው ከገዳማቸው መድረስ ይኖርባቸዋል... እናም ወደዚያው ተፋጠኑ... ብዙ ተጉዘው ከገዳማቸው በር ሲደርሱ አንደኛው መነኩሴ ሴቲቱን ለረዳት ባልንጀራው እንዲህ አለው... "ቅድም ግን ሴቲቱን መንካትህ ልክ ነበር?... እንዴት መነኩሴ ሆነህ ይህን ታደርጋለህ?" ... በዚህ ወቅት ተወቃሹ አስገራሚ ምላሽ ሰጠ... "ልክ ነህ ሴቲቱን ከወንዙ አውጥቻታለሁ... ገላዋንም ነክቻለሁ... ሆኖም እዚያው ወንዙ ዳር ትቻት መጥቻለሁ... አንተ ግን በልብህ እዚህ ድረስ ተሸክመሃታል" አለው... ህም...
___

ወንዙ ዳር ጥለናቸው ልንመጣ ሲገባን እስከ መቃብራችን አፍ ተሸክመናቸው በመጡ ኮተቶች ምክንያት ስንት ዘመን በድንግዝግዝ ተጓዝን?... ከወንዙ ዳር ባልተውነው ቂም ምክንያት ስንቴ ከበደሉ የሚልቅ ህመም ዕድሜ ዘመናችንን በላው?... ስንት ከፍታዎች ላይ ልንገኝ ስንችል... ስንት የስኬት ማማ ልንወጣ ስንችል... በሕብር - በድምር - በጥምር ልንቆም - ባለጋራችንን ድል ልንነሳ ስንችል... ስንቴ እጅ ሰጠን?...
___

የወዳጄን "የአፍታ እንከን" በዕድሜ ልክ በጎነቱ የለወጥኩ ዕለት ታመምኩ... እርሱ ይቅርታ ጠይቆኝ ሰላሙን አግኝቷል... ግና እኔ እርሱን ባሰብኩ - ባየሁት ቁጥር ቁጣዬ እያገረሸ... ቂም እያቃረኝም እያቃቃረኝም እኖራለሁ...
___

መድረሻዬ ሩቅ ቢሆንም በጓዜ ብዛት የነብር ፍጥነቴን በኤሊ ጉዘት ለውጬ እንገታገታለሁ... በመንገዴ በሰረገላቸው ያስቀመጡኝ ነበሩ... ሆኖም አካሌ ከመቀመጫው ሲውል ሸክሜ ከአናቴ አልወረደም ነበር...
___

ወንዙ ጋ እያለሁ ላደርግ እችለው በነበረ ጥቂት ደግነት ብዙ ውድመት ማስቀረት እየቻልኩ በማለፌ ጸጸት እያኘከኝ እልፍ ጸሐይ ጠልቋል... በወቅቱ ባልሰነዘርኳት በጎ ቃል ምክንያት - ብዙ ልቦች ተጎድተዋል... በወቅቱ ባልዘረጋሁት ክንዴ ምክንያት - ብዙ ጎጆዎች ፈርሰዋል... በወቅቱ ባልደፈንኳት ቀዳዳ ምክንያት - ግዙፍ መርከቦች ሰምጠዋል... በወቅቱ ባላከምኳት ቁስል ምክንያት - ሙሉ አካል ተመርዟል...
___

እነሆ ውብ ቃል...

"The time is always right to do the right thing." ~ Martin Luther King
___

ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ
242 views17:23
Open / Comment
2022-03-28 01:52:52
212 views22:52
Open / Comment
2022-03-24 06:34:27 If you don't feed me, you won't starve me.
If you don't motivate me, your harsh words won't hurt me.
If you didn't create me, surely, you won't destroy me.
― Mitta Xinindlu
@quoteitq
256 views03:34
Open / Comment
2022-03-20 21:18:52
He is not heavy, he is my brother.
288 views18:18
Open / Comment
2022-03-11 23:27:52
@Quoteitq
294 views20:27
Open / Comment
2022-03-11 13:39:25
284 views10:39
Open / Comment