Get Mystery Box with random crypto!

Invitation/Call for Volunteer Environmental Lawyers or/ and En | Opportunity 4 Lawyers

Invitation/Call for Volunteer Environmental Lawyers or/ and Environmentalists

ለበጎ አድራጊ የአካባቢ ተቆርቋሪዎችና ለአካባቢ ሕግ ባለሙያዎች የቀረበ ግብዣ - ጥሪ


ድርጅታችን ቁም ለአካባቢ - Defend the Environment ሕግን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከ2ኛ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ በተማሩና በየዘርፋቸዉ ከፍተኛ ዉጤት ባስመዘገቡ ግለሰቦች የተመሰረተ እና በመልካሙ ኦጎ የሕግ ቢሮ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት /fully funded by Melkamu Ogo Law Office/ ቦርድ መር ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ የሲቪል ማህበረሰብ - ድርጅት /NGO/ ነዉ፡፡ 

ይህ ጥሪ የተደረገዉ የትምህርት ዝግጅታቸዉ የአካባቢ ሕግ - Environmental Lawyers ወይም ለአካባቢ ተቆርቋሪ በመሆን አካባቢ እንዲጠበቅና እንዳይበከል በተለያዩ መንገድ ለሰሩ - Environmentalists እና ድርጅታችንን በበጎ አድራጊ ባለሙያነት /Volunteer Professionals/ ለማገልገል ለሚፈቅዱ ሰዎች ከዘርፉ ጋር በተገናኘ በሚሰራ ድርጅታችን ምስረታ መርሃ ግብር ላይ በሚቀርቡ የጥናት ጽሁፎችና የዉይይት መድረክ ላይ መገኘት የሚያስችል እና የበጎ አድራጊነት ስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ዕድል ለማመቻቸት በማሰብ ነዉ፡፡ 

ለዚህ ድርጅት መመስረት ምክንያት የሆኑት ጉዳዮች በርካቶች ቢሆኑም በዋናነት:- 

አከባቢን /Environment/፣ ብዝሃ ህይወትን /Biodiversity/ እና ተፈጥሮ ሀብትን /Natural Resources/ መንከባከብን፣ ጥበቃ ማድረግን፣ 

የአከባቢ ብክለት /Pollution/ መቀነስ/ማጥፋትን፣ 

የታዳሽ ኃይል /Renewable Resources/ አገልግሎት ማስተዋወቅን፣

ለአየር ንብረት ለዉጥ /Climate Change/ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን መቀነስ/ማቆምን እና

መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ጥበቃ - Protection of Fundamental rights and freedoms ስራዎችን

በተመለከተ ጥናት እና ምርምር ማድረግ፣ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች/ባለሙያዎች ለአቅም ግንባታ የሚሆን የስልጠና፣ ትምህርት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ማዘጋጀት፣ ለአከባቢ ጥበቃ ምቹ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁና በስራ ላይ ያሉትም ለዚሁ ተግባር እንዲመቹ ተደርገዉ እንዲሻሻሉና የማያስፈልጉ ሕጎች እንዲሻሩ ምክረ ሃሳብ ማቅረብ እና አፈጻጸማቸዉን መከታተል /Legal Monitoring/፣

እንዲሁም በዋናነት አከባቢን በሚበክሉ፣ በተፈጥሮ ሃብት እና በብዝሃ ህይወት ላይ በማናቸዉም ሁኔታ ጉዳት በሚያደርሱ ሰዎች/ተቋማት ላይ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በሚቀርቡ  የሙግት አቀራረብ/አመራር ስርዓት /Environmental Public Interest Litigation/ በመከተል ክሶችን በፍርድ ቤት እና በአስተዳራዊ አካላት ዘንድ በማቅረብ የህዝብን ከብክለት በጸዳ እና ንጹህ በሆነ አከባቢ በመኖር ጤንነቱን መጠበቅ የሚያስችለዉን ዕድል መፍጠር ነዉ፡፡  

ከዚሁም ጋር በተገናኘ የድርጅቱ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ በሀገራችን በስፋት ባልተለመደዉ በዚህ አይነቱ የሙግት ስርዓት በመጠቀም አከባቢን ሲበክሉ በነበሩ ተቋማት ላይ ክሶችን/አቤቱታዎችን በፍርድ ቤት እና በሚመለከተዉ አስተዳደራዊ አካል ዘንድ በማቅረብ ለጉዳዩ የተለያየ ዉጤት ያስገኙና ሕዝብ ነገሩን እንዲገነዘብ እንዲሁም የመንግስት ትኩረት እንዲያገኝ አድርገዋል፡፡ 

በመሆኑም ይህ ድርጅት የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት ይረዳ ዘንድ ከተነሳንበት ጉዳይ ጋር በተገናኘ በዘርፉ ጥናት እና ምርምር ያደረጉ እዉቅ ምሁራን የጥናት ጽሁፍ በማቅረብ በዘርፉ ያለዉን ሁሉን አቀፍ ክፍተት እንዲያሳዩ፣ የድርጅቱን መቋቋም ለህዝቡ በማሳወቅ ከአከባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ ጥፋት ፈጻሚዎችን በመጠቆም መረጃ እንዲሰጡን ለማስቻል፣ ከድርጅቱ ጋር ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸዉ አካላት ጋር አብሮ ለመስራት ትዉዉቅ ለማድረግ እና ከተሳታፊዎች ጋር ገንቢ ዉይይቶችን በማድረግ ዉጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል መድረክ በግንቦት 07 ቀን 2013 ዓ.ም ቦሌ ኤድናሞል ጀርባ በሚገኘዉ Best western international Plus Hotel ከጠዋቱ 2፡30  – 6፡30 ሰዓት በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ድፕሎማቶች፣ ምሁራን፣ የሕግ ባለሙዎች እና ሌሎችም ተጋባጅ እንግዶች በሚገኙበት ለማሰናዳት ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ 

በመሆኑም፡-

የትምህት ዝግጅታቸዉ ከአካባቢ ሕግ /Environmental Law/ ጋር በእጅጉ የተገናኘ ወይም

ከአካባቢ ጋር በተገናኘ በፍርድ ቤት እና/ወይም በአስተዳራዊ አካላት ላይ ከሶስት ባላነሱ ክሶች/አቤቱታዎች /Environmental litigation/ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ወይም

የአካባቢ ተቆርቋሪ በመሆን በማናቸዉም መንገድ የሚታይ አበርክቶት ያላቸዉ /Environmentalists/ እና

ድርጅታችን ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚያቀርባቸዉ ክሶች/አቤቱታዎ ላይ በበጎ አድራጊ /volunteer/ ባለሙያነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆኑ 4/አራት ሰዎችን በዕለቱ መድረክ ላይ እንዲገኙ የሚያስችል ዕድል ተመቻችቷል፡፡

ስለሆነም ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 ከተጠቀሱት መስፈርቶች አንዱን እና 4ተኛዉን ማሟላት የምትችሉ ሰዎች የድርጅቱ መስራች እና የቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት አቶ መልካሙ ኦጎ (የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ) ሥም እና አድራሻችሁን ከስር ከሚቀመጡ አድራሻዎች በአንዱ በቅድሚያ በመላክ የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ትችላላችሁ፡፡ ቀድሞ የደወለ/የጠየቀ ዕድሉን ቀድሞ የሚያገኝ መሆኑ ይታወቅ፡፡


Melkamu Ogo – Cellphone - +251 911 02 71 03, E-Mail - andiracha16@gmail.com or info@melkamuogo.com,     Website – www.melkamuogo.com 

     

ፍትህ ለአካባቢ - Justice for the Environment.