Get Mystery Box with random crypto!

የበዓል መልዕክት : በየትኛውም የምድር ክፍል የምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን | ORDI GRAPHICS

የበዓል መልዕክት :

በየትኛውም የምድር ክፍል የምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለትንሳዔ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ ከክፉ ድርጊት እና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በዚህ በዓል፦ ከጎናችን የተለዩ ንፁሃን ወገኖቻችን እያሰብን፣ ከቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ የወደቁትን ፣ የሚወዱትን ተነጥቀው በሀዘን ላይ የሚገኙ ቤተሰቦችን ፣ በሰላም እጦት ከሚኖሩበት ከቄያቸው ተሰደው በሰው ሀገር የሚንከራተቱትን ወገኖቻችን ፣ በየሆስፒታሉ የታመሙትን እያሰብን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

በተጨማሪም በዓሉን ስናከብር በየዕለቱ የዜጎቻችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል እንዲሆን አደራ እንላለን ፤ ከተቻለ ከቤታችን ሳንወጣ እናሳልፍ ፤ መንቀሳቀስ ግድ የሚለን ከሆነ / ዘመድ ጥየቃ፣ ወዳጅ ጓደኛ ስንሰበሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እናድርግ።

የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የበረከት በዓል ያድርግልን!
ሀገራችን ሰላም ያድርግልን!
ፈጣሪ የሰው ልጆችን ሁሉ ይጠብቅልን።

መልካም የትንሳኤ በዓል #ordigraphicsfamily !