Get Mystery Box with random crypto!

አቡበከር ቃሲም እባላለሁ፣ ከ MS ህመም ጋር ከ 6 አመት በላይ ኖሬያለሁ፣በበሽታው ምክንያት በ አ | Paraphernalic Thoughts

አቡበከር ቃሲም እባላለሁ፣ ከ MS ህመም ጋር ከ 6 አመት በላይ
ኖሬያለሁ፣በበሽታው ምክንያት በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ 3 ኛ
አመት ኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ ትምህርቴን ማቋረጥን ተገድጃለሁ፤
በሽታው በአፍሪካና በምድር ወገብ ዙሪያ በሚገኙ ሀገራት ላይ
የመከሰቱ እድል አናሳ ነው፤በሽታው ከተከሰተ እንደ አውሮፓዊያን
አቆጣጠር 1868 ጀምሮ በባለሙያዎች ብዙ ጥረት ቢደረግም ፍቱን
መድሀኒቱ አልተገኘለትም ፤ነገርግን ለበሽታው ህክምና የሚውሉ
መድሀኒቶች ይሰጣሉ፤ እኔ እና የማህበሩ አባላት ረጅም ግዜ
ቢፈጅብንም እስከ 20 የሚደርሱ MS ህሙማንን ማግኘት ችለናል ፤
እንዲሁም"የ መልቲፕል ስክሎሮሲስ ህሙማን መርጃ በጎ አድራጎት
ማህበር"ን መስርተናል፤ ከመሰረትንበትም አላማዎች ውሰጥ እነዚህ
ይጠቀሳሉ:―
―ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ስለ በሽታው ግንዛቤን ማስፋት

―ለ MS ተጠቂዎች የአቅምና የስነ ልቦና ድጋፍ ማድረግ፤
―ከባለሙያዎች ጋር በመተባበር ስለ MS የቆመ የ ፊዝዮቴራፒ
ማዕከልን መክፈት፤እንዲሁም
―ለ MS ህሙማን የህክምና ድጋፍ ማድረግ፤ይገኙበታል።
ነገርግን ለህክምና የሚውሉ መድሀኒቶች ሀገራችን ውስጥ አለመኖሩ
እና ከሌላም ሀገር ለማስመጣት ዋጋቸው ውድ በመpoሆኑ እኔ እና
ማህበራችን ውስጥ የምንገኝ አባላት በበቂ ሁኔታ ህክምናውን
መከታተል አልቻልንም፣ከህክምናው በተጨማሪ አሰፈላጊ በሆኑ
ጉዳዮች ላይ ትብብራችሁን በትህትና እንጠይቃለን።
://www.facebook.com/MSiEth/