2021-04-27 20:46:38
ሰበር መግለጫ
➥ ለጠቅላይ ሚነስትር ፅ/ቤት
➥ ለ ትምህርት ሚነስትር
➥ ለ የሀገረ አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ
➥ ለ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት አግባብነት ጥራት ካውንስል
➥ ለ ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር
➥ ለተለያዩ የሚዲያ አካላት
ጉዳዩ :- የ 2012/2013 የ 12ኛ ክፍል
ከፍተኛ ተቃውሞን ስለማሳወቅ እና
መፍትሔን ስለመጠየቅ ይመለከታል ።
እኛ ማለትም የ2012/2013 የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወሳጆች በተደረገው ኢ-ፍትሃዊ እና አድሎአዊ ተግባር ድምፃችንን ከፍ ብሎ እንዲሰማ እንፈልጋለን ። 15 ዓመት ሙሉ ሃሳባችንን በነጻነት ሠላማዊ በሆነ መልኩ መግለፅ እንደምንችል ለቅሬታችንም ተገቢውን እና አስፈላጊውን መልስ ማግኘት እንደምንችል ስነዜጋ እና ስነምግባር ባሉት ትምህርት ሲነገረን ኖረዋል። እኛም ይህን መሠረት አድርገን ግዴታችንን አሞልተን መብታችንን ማስከበር ይገባናል ብለን ተነስተናል ።
ከዚህ ጋር በተያያዘም ተማሪዎች በከፍተኛ መልኩ ከ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ያወጣው የዩኒቨርስቲ መቁረጫ እና የግል መማሪያ ውጤት ከታች የተዘረዘሩትን ከፍተኛ ችግሮችን ያየና ያገናዘበ አይደለም ።
ችግሮችና የተማሪ አቤቱታዎች እንደሚመለከተው ቀርበዎል:-
1ኛ በኮሮና ጉዳይ ....
በኮሮና ምክንያት ያለ አስተማሪ ፤ ከጓደኞቻችን የከበደንን ሳንጠያየቅ ለብቻችን ...በግል ጥረት ለማንበብ ጥረናል ። በቲቪ ተማሩ ተብለንም የፕሮግራሞች መዛባት , የወጥነት ችግር , የኮሮና ጭንቀት ወዘተ እንዳንከታተል እንዳረገን እየታወቀ ። ተፅህኖውም ምንም ከቁብ አለመቆጠር። በተለያዩ የማሕበራዊ ድሕረ ገጿች ተፅእኖ ።
2ኛ ማካካሻ ዙርያ ...
አንድም ሞዴል አለመፈተን ፤ 45 ቀን ማካካሻ በሚል ታች ባልወረደ ነገር አለባብሰው ለ7/8 ወር ከት/ት መራቅ ።በየገጠር ትምህረት ቤቶች ሙሉ በሙሉ አለመማር ። የትምህርት በ ቤቴ መርሐ ግብር ሁሉንም ያካተተ አለመሆኑ ። በስርጭቱ ያሉ ችግሮች እንዳሉ ሆነው ።ትምህርት ሚኒስቴር ምን አስቦ ነው
3ኛ የመራዘም ጉዳይ ...
ለ4 ግዜያት ፈተና መራዘም ፤ ባልገባ ታብሌት ሊፈትኑን ቀን ቆርጠው ተዘጋጅተን መቀያየር ሀምሌ 15፤ መስከረም 30 ታህሳስ 24፤ ጥር መጨረሻ እየተባለ መራዘም። አራት ግዜ መራዘም ።
በተማሪ የቀረቡ ሀሳቦችና ቅሬታዎች
1, ከነበረዉ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ቢያንስ የማለፊያ ነጥቡ በፊት ከነበሩት የማለፊያ ነጥቦች ያነሰ መሆን አለበት!
ምክንያቱም
1.1 በሀገራችን በነበረዉ አለመረጋጋት
1.2በኮረና ቫይረስ ምክንያት እቤት በስጋት ለወራት መቀመጣችን
1.3የፈተና ግዜዉ ከ4 ግዜ በላይ መራዘም
1.4የትምህርት ቤት የዝግጅት እጥረት
1.5የተማሪዎች አዕምሮ ቀዉስ ዉስጥ መግባት
ወ.ዘ.ተ ሲሆኑ
ይህ ሁሉ ምክንያት ባለበት እንዴት ነጥብ ሊጨምር ይችላል?
በ2011 ባች በሀገሪቱ አለመረጋጋት ምክንያት ተብሎ የማለፊያ ነጥብ ከግማሽ በላይ ወርዶ ነበረ
የዘንድሮ አመት ከበቂ በላይ ምክንያት እያለ መቀነስ ሲገባዉ እንዴት ከግማሽ በላይ ሊጨምር ይችላል?
2, ለየግል ተቋማት ማለፊያ ነጥብ መቀነስ አለበት
ምክንያቱም 3 አመት ቀልድ አይደለም ለዲኘሎማ ከታሰበማ ከ10 ጀምሮ ተምረን አሁን ስራ ይዘን ዲግሪ በግል እንማር ነበር እስከ 12 ድረስ መሄድ ባላስፈለገ ነበር ቤተሰብ ከልጆቹ ብዙ ይጠብቃል
3, ስለፈተናዉ አፈታተን ቁጥጥር በጥልቀት ይፈተሽልን
3.1 ፈተናዉ መሰረቁ
3.2 አስተማሪ ሰርቶ ለተማሪ መልስ መስጠቱ
3.3 ተማሪዉ ያለምንም ፍርሃት ኩረጃን እንደ ዲሞክራሲያዊ መብት በመመልከት አስተማሪዉ ተማሪዎች በነፃነት በህብረት እንዲሰሩ መፍቀድ
3.4 ተማሪ ስልክ ይዞ እስከ መግባት ቸልተኝነት የተሞላበት የፈተሻ አካላት ና በገንዘብ ስልክ የሚያስገቡ አካላት መኖር
4. internet አገልግሎት አለመቋረጥ
4.1 የተሰረቀዉ መልስ እንዲሰራጭ አድርጓል
ትምህርት ሚንስተሩ ይህንን ሚዛናዊ ማድረግ ይኖርበታል
''የማትኖሩበትን ፍትሀዊነት አታስተምሩን!!''
ቅሬታዎች እና አቀራረባቸው
1 :- ደብዳቤ በማስረጃ ማስገባት በፎቶግራፍ
በቪድዮ ወዘተ
2 :- በቀጥታ ከፍተኛ አካላት እንዲያዩት ማድረግ
ሚኒስትሩ እናም የበታች አካላት
3 :- በፍጥነት ለውሳኔ እንዲደርሱ ጥያቄ ማቅረብ
አቀራረባቸው
➥ መገናኛ ስፍራ ካሳንቺስ ከ INTER CONTINUTAL HOTEL ከፍ ብሎ በሚገኝው የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ።
➥ ሰዓት 2:30
መደረግ ያለባቸው ነገሮች
➥ እኛነታችንን ሚገልፅ መታወቂያ
➥ አፍ መሸፈኛ ማስክ
➥ ሳኒታይዘር
➥ በተቀናጀና በማስረጃ የተደገፈ
እና በሰላማዊ መንገድ ይሆናል ።
ፍትሕ ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ።
191 views17:46