🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ትዳር ከባድ ነው። ፍቺም ከባድ ነው። የቱ ከባድ ይሻልሀል/ሻል? ገንዘብ ማጣት ከባድ ነው። ከ | SAFE LIGHT INITIATIVE

ትዳር ከባድ ነው።
ፍቺም ከባድ ነው።
የቱ ከባድ ይሻልሀል/ሻል?

ገንዘብ ማጣት ከባድ ነው።
ከምትፈልገው ቀንሰህ ገንዘብ መቆጠብም ከባድ ነው።
የቱ ከባድ ይሻልሀል/ሻል?

ከሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖር ከባድ ነው።
ከሰዎች ተለይቶ መኖርም ከባድ ነው።
የቱን ከባድ ትመርጣለህ/ጫለሽ?

ውፍረት ከባድ ነው።
ውፍረት ለመቀነስ ጠዋት ተነስቶ መሮጥም ከባድ ነው።
የቱ ከባድ ይሻልሻል/ሀል?

ሕይወት ቀላል አይደለችም!
ሁሌም ከባድ ምርጫዎች አሏት!
ግን የሚሻለንን ከባድ የመምረጥ መብት አለን።