Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ቀን ለብዙዎቻችን ትልቅ ቀን እንደሆነ አስባለው:: እንደ ሀገር ያሉንን የህብረተሰባዊ እሴቶች | SAFE LIGHT INITIATIVE

ይህ ቀን ለብዙዎቻችን ትልቅ ቀን እንደሆነ አስባለው:: እንደ ሀገር ያሉንን የህብረተሰባዊ እሴቶች ከምንፈትሽባቸው ክንውኖች መሀል አንዱ ነው:: የሰው ልጅ የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence) እንደሚያስፈልገው ሁሉ ማህበራዊ ብልህነትም (Social Intelligence) እንደሚያስፈልገው በዘርፉ ጥልቅ ጥናት ያካሄዱት ዶ/ር ዳንኤል ጎልማን (Dr. Daniel Goleman) Daniel Goleman በሰፊው #Social_Intelligence በሚለው መፅሐፋቸው ያትታሉ::

ምርጫ ወሳኝ ነገር ነው:: ነገር ግን ያለን ማህበራዊ ትስስር ከምርጫውም በላይ እጅጉን የላቀ ነው:: ከምርጫው በሗላ የሚኖረንን ማህበራዊ መስተጋብር አደጋ ውስጥ የሚከት ከሆነ እንደ ሀገር ማህበራዊ ብልሀት (Social Intelligence) የለንም ማለት ነው:: አዕምሮችን የተባረከ ነው:: አንዳችን ከሌላችን ተስማምተን የምንኖርበትን የአንጎል ሆርሞን በሚገባ በማመንጨት ሚዛናዊ እይታ እንዲኖረን ያግዛል:: ከፊት ለፊታችን እጅጉን የእኛን የሰከነ አካሄድ: የበሰለ ምላሽና የሰለጠነ ውሳኔዎች የሚጠይቅ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን::
ማህበራዊ እሴቶቻችንና ትርክቶቻችን የሚጠቅሙን እዚህ ጋር ነው:: እኔ ትብስ አንተ ትብስ ተባብለን ዓለምን ጉድ የምናስብልበት ከሰሜን እስከ ደቡብ: ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በአንድነት ዜማ የምንቃኝበት ይሆን ዘንድ እነሆ ራሳችንን ለማዘጋጀት ይህን የእውቀት ማዕድ እንካቹ እላለው:: በእዚህ ሳምንት ይህን ታነቡ ዘንድ ጋበዝኩኝ::
ሰላምና ጤና ለሁላችሁም::

ስለሺ ሳልስ ዑመር
የሴፍ ላይት መስራችና ዳይሬክቶር
#BookRecommendation
#BookForTheWeek
#InspireEmpowerTransform
@SafeLightOfficial