🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ውድ ኢትዮጵያዊያን! ውድ የሀገሬ ልጆች ኢትዮጵያ በወጣቶች የዩናይትድ ኔሽንስ (Model United | SAFE LIGHT INITIATIVE

ውድ ኢትዮጵያዊያን! ውድ የሀገሬ ልጆች ኢትዮጵያ በወጣቶች የዩናይትድ ኔሽንስ (Model United Nations ) መድረክ አስደናቂ ድል አስመዝግበዋል!
Congratulations!!
ከ50 ሀገራት በላይ በቱርክ ኢስታንቡል በነበረው ትልቅ ኮንፈራንስ ከነበሩት ሽልማቶች 75% የሚሆነውን ጠቅልለን ወስደን የሀገራችንን ሰንደቅ በዓለም ዐቀፍ መድረክ ላይ ከፍ አድርገን አውለብልበናል!!
እኔና ኤደን ደረጀ #በምርጥ_የዩናትድ_ኔሽን_ተወካዮች (#Best_United_Nations_DELEGATE ከሁለት የተለያዩ ኮሚቴዎች ማለትም ከዓለም ጤና ድርጅት ኮሚቴ(WHO Committees) እና የዩናይተድ ኔሽንስ የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር (United Nations Higher Commissioner for Refugees UNHRC) ትልልቆቹን ሽልማቶች ስንጎናፀፍ
ምህረት ሂሩይ #በምርጥ_ዲፕሎማት (#Best_Diplomat_Award) ሀገራን አኩርታለች::
#በምርጥ_የክብር_ዲፕሎማት (#Honorable_Delegate_Award ወንድማችን አብዲዋሊ ለሀገራችን ድልን አስመዝግቧል!!!
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ተወካዮች በነበረን ግዜ ተወዳጆች ድምቀቶችና ከምንም በላይ እኛ ኢትዮጵያውያን ምንም እንኳን በየትኛውም ችግሮችና ውጣ ውረዶች ብናልፍም ትልቅ ተስፋ ያለን ህዝቦች እንደሆንን አረጋግጠናል!!!
አሁንም እንኳን ደስ አላችሁ!!!
#InspireEmpowerTransform
#MUN
#FLMUN
#Victory
@SafeLightOfficial