Get Mystery Box with random crypto!

የወጣቶችን የአመራር ክህሎት ለማዳበር ታስቦ የተዘጋጀው ኮንፈረንስና ውድድር በትላንትናው ዕለት ተጠ | SAFE LIGHT INITIATIVE

የወጣቶችን የአመራር ክህሎት ለማዳበር ታስቦ የተዘጋጀው ኮንፈረንስና ውድድር በትላንትናው ዕለት ተጠናቋል

በማጠቃለያ መድረኩ ተገኝተው  መልእክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ክብርት ሙና አህመድ እንደገለጹት፥
" የተከናወነው የወጣቶች የአመራር ክህሎት ውድድርና ኮንፈረንስ  የሀገራችንን የወደፊት  መሪዎች በአለም አቀፍ ና አህጉራዊ መድረክ ላይ በእውቀትና በበሳል የአመራር ጥበብ  እንዲያድጉ መሰረት የሚጥል ሲሆን  ኮንፈረንሱ ወጣት መሪዎች ወደፊት የሀገርን ጥቅም የሚያቀርቡበት እና ሀሳባቸውን የሚገልጹበትን እውቀት የያዙበት በመሆኑ ፋይዳው የጎላ ነው"
ሲሉ ገልጸዋል።

የተከበሩ ሚኒስቴር ደኤታን ላሳዩት እጅግ  ትብብርና የአመራር መንፈስ ድርጅታችን ሴፍ ላይት በመስራችና ስራ አስኪያጁ አምባ/ስለሺ ሳልስ ዑመር በኩል ያለውን ላቅ ያለ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን አሁንም ለሀገራችን የወደፊት ብልፅግና እና እድገት ፈር ቀዳጅ በሚሆኑ መሠል ትውልድ ገንቢ ስራዎች ላይ ባላሰለሰ ጥረት ለመንቀሳቀስ ያለውን ቁርጠኝነትና ቅንጅትን በሚጠይቁ መስኮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ ለመስራት ያለውን ፍላጎት ለመግለፅ ይወዳል።

ለመሠል አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች የሴፍ ላይት ቤተሰብ ይሁኑ
       #InspireEmpowerTransform

www.safelightet.org
 
@SafeLightOfficial

#Lets_Met_The_Goals #LCC
#ProEthiopian #ProAfrican #MOWSA #LCC2022
#MUNSimulations
#GreatEthiopianDam2022
#BeTheVoice #LetsResolve
#SAFELIGHTSUMMER2022
#BuildingFuture #GlobalMindset
#Transform2032 #Model2053 #Agenda2063