🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ሀኪማችንን እናሳክመው ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ እባላለው። በ2015 ከአ.አ.ዩ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታ | Sarcasm

ሀኪማችንን እናሳክመው

ዶ/ር ሳምሶን ይስሀቅ እባላለው። በ2015 ከአ.አ.ዩ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ሙያ ትምህርት የተመረቅሁ ስሆን ለስድስት ወራት በጠቅላላ ሀኪምነት ወገኔን ሳገለግል ቆይቻለሁ።

ድንገት ሚዛኔን ስቼ መውደቅ እና ሌሎችም ምልክቶችን በማሳየቴ ወደ ጤና ተቋም ተጉዤ ምርመራዎችን ካደረግኩ በኋላ የጭንቅላት እጢ እንዳለብኝ ተነገረኝ። የናሙና ምርመራም ተደርጎ Grade III Astrocytoma እንዳለብኝ ተነግሮኛል።

እኔን ትልቅ ቦታ ደርሼ ማየት ለሚመኙት ቤተሰቦቼና ከኔ በታች ላሉት እህት ወንድሞቼ ዜናው በጣም ትልቅ ዱብዳ ነው የሆነባቸው።

የጥቁር አንበሳ የጭንቅላት ቀዶ ጥገና ሀኪሞች ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ ህክምና ማድረግ እንዳለብኝ ወስነዋል። ለሕክምናውም እስከ 2.3 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ተነግሮኛል። ሕክምናው ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ስለሆነ በመንግስት ሰራተኛ የሀኪም ደሞዝም ሆነ በቤተሰቦቼ አቅም የምንችለው አይደለም።

እባካችሁ ተገቢውን ሕክምና ማግኘት እችል ዘንድ የቻላችሁትን ትረዱኝ ዘንድ በፈጣሪ ስም እጠይቃለው። በየ ሃይማኖታችሁም ፈጣሪ በመንገዴ ሁሉ እንዲረዳኝ በጸሎታችሁ እንድታስቡኝ እጠይቃችኋለሁ።

የበኩሎን እገዛ ለማድረግ የሚከተሉትን አካውንት ቁጥሮች ይጠቀሙ፡
Samson Yishak Beyene
ንግድ ባንክ: 1000139965691
አዋሽ ባንክ: 013201172039000
Birhane Beyene Mideksa (እናት)
ንግድ ባንክ: 1000549927681
አዋሽ ባንክ: 01347903970500

ቤተሰቦቹን ማግኘት የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠው ስልክ ወላጅ እናቱን ማግኘት እና ማናገር ትችላላቹ።
+251911353752 ብርሀኔ በየነ

@Thequorachannel

Share