ዩኒቨርሲቲው ለ2016 የትምህርት ዘመን ከጥር ወር ጀምሮ 11 ሺህ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሆኑ የመመገቢያና ማደሪያ ክፍሎች እንዲሁም በቤተ- መጽሐፍትና በሌሎች አገልግሎት መስጫ ስፍራዎችም ዝግጅት ማድረጉን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ይኸይስ አረጉ (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡
"በክልሉ በሚፈጠር የፀጥታ ችግርና የመንገድ መዘጋት ለዩኒቨርሲቲው የሚያስፈልገው የምግብና የቁሳቁስ ግብዓት እጥረት እንዳያጋጥም አስፈላጊው ጥረት ይደረጋል" ብለዋል።
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለነባር እና አዲስ የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎቹ ከጥር 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሪፖርት ማድረጉ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ( ጥሪው፦ https://t.me/TikvahUniversity/9834)
@tikvahuniversity