Get Mystery Box with random crypto!

ብዕሬ ፀብ አይመርጥም! # ሀሰትን እና ሀሰተኞችን ይወጋል። ድል ለ ብዕሬ!! (ኦፍታኤ ዳዊት ቶሬ) | የኛ🔊

ብዕሬ ፀብ አይመርጥም! # ሀሰትን እና ሀሰተኞችን ይወጋል። ድል ለ ብዕሬ!!
(ኦፍታኤ ዳዊት ቶሬ)
ኢሬቻ!!
ኢሬቻ ወርቃችን ነው እንደምቅበታለን እንኮራበታለን!!
ኢሬቻ የ ኦሮሞ ሕዝብ ካለው ክብረ በዓል በጣም ትልቁ እና ዋነኛው ነው።
ኢሬቻ በሁለት ይከፈላል። እነርሱም ኢሬቻ መልካ እና ኢሬቻ ቱሉ ናቸው።
1, ኢሬቻ መልካ ክረምት ሲወጣ እና ፊቱን ወደ በጋ ሊዞር እና በበጋ ሊተካ ሲል
በክረምት ዝናብ ሰቶ፡ ልምላሜ አድርጎ ወንዞችን ሁሉ ሞልቶ በክረምት ፀጋው
የሰውን ልጅ እና ፍጥረትን ሁሉ ያጠገበውን ወይም ያስደሰተውን አምላክ
እንዲሁም የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ የሆነውን ፈጣሪ( ዋቃን) የኦሮሞ ሕዝብ
ሁሉ ወደ ውጪ ወጥቶ ፍጥረትን እየተመለከተ አምላኩን የሚያመሰግንበት፡
ትልቅ ክብረ በዓል ነው።
በአጠቃላይ ኢሬቻ መልካ የምስጋና ክብረ በዓል ነው።
2. ኢሬቻ ቱሉ= ኢሬቻ ቱሉ ልክ በክረምት ወቅት ቸርነቱን፡ ሰጪነቱን፡ ለጋስነቱን፡
አዛኝነቱን ከፍጥረት ሳያርቅ በጎነትን እና መልካምነትን ለፍጥረት ሁሉ ያሳየ
ፈጣሪ ልክ በክረምት ወቅት እንክብካቤውን ጥበቃውን ለእንስሳውም ለሰውም
ልጅ ሁሉ አድርጎ ያሳለፈ አምላክ አሁንም በበጋ ጊዜ ከፍጥረት ሁሉ ቸርነቱ
እንዳይርቅ ምህረቱ ፀንቶ እንዲኖር ወንዞች እንዳይደርቁ ዝናብም እንዳይጠፋ
( ልብ በሉ ዝናብ ጠፋ ማለት ድርቅ ይከሰታል በዚህ ምክንያት ደግሞ የሰው
ልጅ ብቻ ሳይሆን እንስሳትም፡ እፅዋትም ሕይወት ስለሚያጡ) ይህ እንዳይከሰት
አባቶች ልክ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የብሉይ ነብያትም፡ በአዲስ ኪዳን አገልግሎትም
እራሱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ተራራ ወጥቶ ይፀልይ እንደነበረው ሁሉ
አባቶችም ተራራ ላይ ወጥተው ልመናቸውን ፀሎታቸውን ወደ ፈጣሪ
ተማፅኗቸውንም ወዳ ሰማይ እና ምድር ፈጣሪ ያደርጋሉ።
በአጠቃላይ ኢሬቻ ቱሉ የልመና የፀሎት ክብረ በዓል ነው።
ታዲያ አንዳንድ አላዋቂዎች ኢሬቻ ጣኦት አምልኮ ነው ብለው ሲሰብኩን ኖረዋል
ኦሮሞ ልክ ዛፍ አምላኪ ወንዝ አምላኪ እንደሆነ እየሰበኩን ለባህላችንም ሆነ
ላለን ፈጣሪን የማመስገን እንቁ የኢሬቻ ክብረ በዓል የተሳሳተ ግንዛቤ
አእምሮአችን ውስጥ እንዲሰረፅ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
የእኛን የሆነ ቋንቋ፣ ባህል እንዲሁም ማንነት ጥለን ባዶ እጃችንን የ ሀሰት
ኢትዮጵያዊነት ውስጥ እንድንኖር አድርገውናል።
አሁን ግን እኛ የተማርነውም በመማር ላይ ያለነውም ትውልድ ቋንቋችንን፡
ባህላችንን እንዲሁም ማንነታችንን በሚገባ አውቀን ተረድተን ለሚቀጥለው
ትውልድ የማስተላለፍ ሚናን መጫወት የእኛ ድርሻ ነው።
ኢሬቻ ወርቃችን ነው እንደምቅበታለን እንኮራበታለን።
@ Ofta'e Daawwit Tooree!!