Get Mystery Box with random crypto!

#DawitNega የአርቲስት ዳዊት ነጋ የቀብር ስነስርዓት ነገ ሰኔ 7 ቀን 204 ዓ/ም ከቀኑ 8 | Zeariaya

#DawitNega

የአርቲስት ዳዊት ነጋ የቀብር ስነስርዓት ነገ ሰኔ 7 ቀን 204 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን እንደሚፈፀም ታውቋል።

አርቲስት ዳዊት ነጋ በህይወት ሳለ " ካሌብ ሾው ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቃለመጠይቅ በሰጠበት ወቅት ለወጣቶች ያስተላለፈው መልዕክት ፦

" ... ስኬት አጠገብህ ነው ያለው። በጣም ሩቅ መስሎ የሚታያችሁ ፣ በጣም ጨለማ መስሎ የሚታያችሁ ነገር ከናተ ጋር ነው ያለው።

ለምንም ነገር መሸነፍ የለብህም። ማንም ሰው የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል በእኔ መማር አለበት።

እኔ ትልቅ ነገር ሰርቼ ሳይሆን በአቅሜ የምችለውን ነገር እየሰራው ነው፤ ቢያንስ ትላንት የምተኛበት ቤት አልነበረኝም፤ ለረጅም ጊዜ የእራት መብያ እንኳን አልነበረኝም እንደኔ ያጣ ኢትዮጵያዊም ያለ አይመስለኝም።

ተስፋ አልቆርጥም። አንድ ጊዜ ሰው ሆናለሁ ብዬ አልሸነፍም ነበር። የ200 ብር የቤት ኪራይ መክፈል ሲያቅትህ አስበው ...

ወጣቱ በእኔ እንዲማር እፈልጋለሁ። የሚፈልገውን ስራ ዶክተር ፣ መሃንዲስ ሊሆን ይችላል የፈለገውን አይነት ሞያ ያለው ሰው እኔ ሰርቼ እቀየራለሁ ብሎ እራሱን ማሳመን አለበት ፤ ከዛ ለራሴ ሆኜ ለሀገሬ ፣ ለህዝቤ ሆናለሁ ብሎ ማሰብ አለበት ፤ ተስፋ ካልቆረጠ ማንም ሰው ምንም ማደረግ ይችላል። "

@tikvahethiopia