Get Mystery Box with random crypto!

በፈረንሳይ የካቶሊክ ቄሶች ባለፉት 70 ዓመታት ውስጥ 216ሺ ሰዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት (አስገድዶ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

በፈረንሳይ የካቶሊክ ቄሶች ባለፉት 70 ዓመታት ውስጥ 216ሺ ሰዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃት (አስገድዶ ደፈራ) ፈፅመዋል። ከተደፈሩት ውስጥ አብዛኃኞቹ ህፃናት ናቸው። ወሲባዊ ጥቃት የመፈፀም ወንጀል የኃይማኖቱ መሪዎች ዘንድ የዚህን ያህል ከተንሰራፋ ተራውን ምዕመን ደግሞ አስቡት?

እስልምና ይህን ዓይነት ወንጀል (ዚና) ለሚፈፅሙ ሰዎች አንድም ሰውዬው እራሱ ዳግም ተመሳሳይ ወንጀል እንዳይፈፅም የሚያስተምር፤ ሁለትም ተመሳሳይ ወንጀል ለመስራት ለሚያስቡ ሰዎች እንዳይሞክሩት መቀጣጫ የሚያደርግ ኮምጠጥ ያለ የቅጣት ህግ አለው። ወንጀሉን የፈፀመው ሰው ያላገባ ከሆነ 100 ግርፋት፤ ያገባ ከሆነ ደግሞ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል።

ይህ ህግ ፈረሳይ ውስጥ ተግባራዊ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ እና የመጀመሪያው ቄስ ደፈራ ሲፈፅም በዚህ ህግ መሰረት ተቀጥቶ ቢሆን ኖሮ፥ ደፈራው የዚህን ያህል ተባብሶ 216ሺ ሰዎች ለደፈራ ባልተጋለጡ ነበር። ጭካኔው መረን አልፎም ህፃናት ሁሉ የዚህ ጥቃት ሰለባ ባልሆኑም ነበር።

ምዕራባዊያን ይህንን ኢስላማዊ ህግ እንደጭካኔ ሲያዩት ያስገርመኛል። ጭካኔ የሚሆነው አንድን ወንጀለኛ መቀጣጫ አድርጎ ብዙ ንፁሃንን የወንጀል ተጠቂ ከመሆንና በወንጀለኞች ከሚደርስባቸው ጥቃት መጠበቅ ሳይሆን ወንጀለኛውን በግዴለሽነት አልፎ የብዙ ንፁሃን ሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ መጣል ነው። ለዚህም ነው ወንጀል እጅግ እየተበራከተ እየመጣ ያለው።

ዓለም ለገባችበት አዘቅት መፍትሔው ኢስላም ነው የምንለው ለዚህ ነው።

https://t.me/Zelebet