Get Mystery Box with random crypto!

አርፍጄ ከነቃሁ በሁዋላ ጉራጌው ጉዋደኛዬን እስቲ ዛሬ መስጂድ ውሰደኝ ብዬ ጠየኩት፡፡ ሳየው በጣምደ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

አርፍጄ ከነቃሁ በሁዋላ ጉራጌው ጉዋደኛዬን እስቲ ዛሬ መስጂድ ውሰደኝ ብዬ ጠየኩት፡፡ ሳየው በጣምደስተኛ ይመስል ነበር፤እኔ ግን ሌላ ምንም አስቤ አልነበረም…በቃ ሁኔታውን ማየት ስለፈለኩ ነበር፡፡

መደወር ገዝቶልኝ ወደ መስጂድ ስንገባ ሰው ሞቶ ነበር፡፡ ወደ ውስጥ ስገባ ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኝ
ነበር፡፡ ጥቂት ቁረአን የሚቀሩ ሰዎችንም ተመልክቼ ነበር፡፡ ታዲያ ውስጥ ኢማሙ አንድ ነገር ተናገረ፡፡

‹አንዱ ወንድማችንን ሲወስድብን አንዱን ወንድማችን ተካልን›ነበር የኢማሙ ንግግር፡፡ ይህን ያለበት
ምክንያት አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ እሱም እኔ ነኝ፡፡

በጉራጌው ጉዋደኛዬ አመካይነት ሳላምንበት ሸሀዳ
ይዤ ነበር፡፡ ሸሀዳ ለመያዝ አስቤ ስላሌድኩ አያያዜ በእምነት ላይ የተመሰረተ አልነበረም፡፡ ውስጤ
ምርምር ለማድረግ ይዳዳው ነበር፡፡ ግን በአንድ አጋጣሚ ደንገት ወደ መስጂድ ብመጣ ሙስሊም ሆኜ
ተገኘሁ፡፡

እስልምናን ተረዳሁት…. ከሰለምኩ ከሁለት ቀን በሁዋላ ረመዳን ገባና መጾም ጀመርኩ፡፡ ለኔ መጾም ከባድ ነገር
አልነበረም፡፡ ምክንያቱም የኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ ከልክ ያለፉ ጾምችን አስተናግድ ስለነበረ፡፡

በኔ የእስልምና ህይወት ውስጥ ወርቃማው ጊዜ ይሄ የመጀመሪያዬ የሆነው ረመዳን ነበር፡፡ ብዙ ዳአዋዎችን
የሰማሁበት፤የሙስሊሞችን የእምነት ጥንካሬ ያየሁበት ነበር፡፡ ለጥቆ ቀጥታ ወደ ቂራት ነበር የገባሁት፡፡

አሊፍ፣ባ፣ታ…ማለት ስጀምር ሁሉም ነገር ተቀየረ፡፡ አስቀድም እስልምናን በቤተሰቡ የተቀበለ ሰው ስለተውሂድ እና ስለአቂዳ ሲወራ ብዙ ግድ ላይሰጠው ይችላል፡፡ ለኔ ግን ልዩ ስሜት ይፈጥርልኝ ነበር፡፡

በእውነት ከአላህ ውጭ በቅንነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) የአላህ
መልዕክተኛ የመሆናቸውን እውነት በሂደት መላ የማቀው ሀቅ ላይ ተንሰራፋ፡፡ ሀቅን ከሀሰት መለየት ጀምሬ ነበር፡፡
ይሄም የሆነው በእስልምና ልዩ ባህሪ ነበር፡፡ እስልምና
እንደማር ነው፤ሲያዩት የሚያስጠላሲቀምሱት የሚጣፍጥ!!!


ይቀጥላል
በድምጽ ለማድመጥ




የተለያዩ ከክርስትና ወደ እስልምና የመጡ የሰለምቴዎችን ታሪክ ያገኙበታል ፦

የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-




AS_HABULE YAMlNE TUBE

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A

አጠር አጠር ያሉ አስተማሪ ቪዲዎች
http://tiktok.com/@as_hbule

የሠለምቴዎች መዝናኛ እና መማሪያ ግሩፕ