Get Mystery Box with random crypto!

መልካሙ አበራ ወይም ዲያቁን ዮሀንስ እባላለው፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ፡፡ በእንዴት ሰ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

መልካሙ አበራ ወይም ዲያቁን ዮሀንስ እባላለው፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ፡፡

በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኬን ላካፍላችሁ ወደድኩኝ ።

እርሱም ወደ ተፈጠርኩበት እምነት እንድመለስ ያደረገኝ አጋጣሚ ቢኖር ። እንዴት ሰለምኩኝ?

‹‹ ብርቱ የሆነ የስላሴ አመለካከት ያለበት ኦርቶዶክስ፡፡ እናት እና አባቴም እንደኔው ኦርቶዶክስ ናቸው፡፡
ኦርቶዶክስ ሲባል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማለቴ ነው፡፡ ሀይማኖቴን ከቤተሰቤ ነው የወረስኩት፡፡
ሀቂቃ ቤተሰቦቼ እንደ ሀቅ በተቀበሉበት እምነት ላይ ጠንካራ አቁዋም ነበራቸው፡፡ ገና በልጅነት ነበር የስለት ልጅ
መባል የጀመርኩት፡፡ የስለት ልጅ መባል የዛን ያህል ቀላል ነገር እንዳይመስላቹ ፡፡

አንድ ልጅ ቤተሰቡን በህመም ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ያስቸግር ከነበረ በሚያምኑበት ታቦት ሁሉ እየተሳሉ ልጁ ሲድን ያዳነው ያ ታቦት እንደሆነ እና ታቦቱን በየደብሩ በአደራ እየተሰጠ እንዲያገለግል ይደረጋል፡፡ እኔም ላይ ተመሳሳይ ነገር ነበር የሆነው፤ገና በልጅነቴ የስለት ልጅነቴን መቀበል እና ታቦት እያገለገልኩ ደብር ከደብር እየዞርኩ
እንደተለመዱት የቅኔ ተማሪዎች ሰው በልቶ የተረፈውን ነገር መብላት ግዴታዬ ነበር፡፡

የተወለድኩት መንዝ ሲሆን ልጅነቴን በሙሉ በቆሎ ትምህርት ቤት ነው ያሳለፍኩት፡፡ ወሎ እስጣይፍ እስጢፋኖስ ገዳም ውስጥ ነው ብዙ ጊዜዬን ያሳለፍኩት፡፡ አባ ገብረ መድህን ለሚባሉ እዛው ገዳም ውስጥ ሞኖክሴ ሆነው ለሚኖሩ ሰው ነበር በቤተሰቦቼ አማካኝነት በአደራ የተሰጠሁት፡፡ ከዚህ ውጭም የተለያዩ ገዳሞች እየዞርኩ የቆሎ ተማሪ ደረጃውን እስኪያገኝ የሚማረውን ትምህርት ሁሉ ወስጃለው፡፡

ግዕዝ አራራይ ዜማዎችን በተለያዩ ደብሮች እየተዙዋዙዋርኩ ተምሬያለው፡፡ ቅኔ አቁዋቁዋም
ለማወቅ ብዙ ለፍቻለው፡፡

ታዲያ በዚህ ሁኔታ አለበቃም፡፡ በተማርኩበት ነገር በተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች በቅዳሴ መምህርነት አገልግያለው፡፡ በአገልግሎት ደረጃ ከሀገር ቤቶች አንስቶ እስከድሬዳዋ ፤ከአሁኑዋ ሲዳማ ክልል አንስቶ እስከ ጂማ፤ከጂማ እስከ ጋምቤላ፡፡ መቼም በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት እየኖረ ነው
ልትሉ ትችላላችሁ፡፡
የቆሎ ተማሪ ምግቡን ለምኖ ነው የሚያገኘው፡፡ ቤቱ ደግሞ መቃብር ቤት ነው፡፡ የተሳሳቱ አመለካከቶች እንደጽድቅ ይቆጠራሉ፡፡ እራስን ዝቅ አድርጎ መኖር ፈጣሪ የሚወደው ነገር ቢሆንም ግን ይሉኝታን ሽጦ መኖር ለኔ ገንዘብ ከማጣት የበለጠ መከራ ነበር፡፡….

መንደርደሪያ…. ‹‹ አንድ አንድን ነገር ከልክ በላይ የጠላ እንደሆን ሀቅ እና አምላክ የወደደለት ነገር ከሆነ
ወደጠላው ነገር መሳቡ አይቀርም፡፡ ለእስልምና ትልቅ የሆነ ጥላቻ ነበረኝ፡፡
ስለ እስልምና አስቀድሞ የነበረኝ አመለካከት የተዛባ እና ከእውነት የራቀ ነበር ፡፡ ታዲያ ልቤ በጊዜ ሂደት እየተረበሸ መጣ፡፡ የኔ የኦርቶዶክስ እምነት አዲስ ሰፈር ገብርኤል ሲደርስ በጃሂሎች አስተሳሰቦች እየተበከለ መምጣት ጀመረ፡፡

ከቤተክርስቲያን ውስጥ የዘር ትርክት እየገባ ሲመጣ እምወደው ጉዋደኛዬ እንኩዋ ምላሱ እየጨነቀኝ
መጣ ፡፡ እኔ ጠንካራ የእምነቱ ተከታይ ስለነበርኩ ይህ ነገር በአንዴ አልነበረም የተፈጠረው፡፡ ግን ሀቅ ውስጥ እንዳልነበርኩ ልቤ ሁሌ ይነግረኛል፡፡

ለረዥም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚደረጉት ነገሮች
ውስጤን ይረብሹት እና ጥያቄ ይፈጥሩበት ነበር፡፡ ግን ሁሉም ነገር አንገሽግሾኝ የማገልገያ ፍቃድ ወረቀቴን ቀድጄ እስክወጣ ድረስ ለኔ ከባድ ነበር፡፡ ታዲያ ከዚህ በሁዋላ ያለፍኩበትን መንገድ መጨረሻሳስበው ከንቱነት ተሰማኝ፡፡ ከዛ በሁዋላ ግን….

ታሪካዊ አመጣጥ….ከቤተክርስቲያን አለም ከወጣሁ በሁዋላ አለማዊውን ህይወት ለመቁዋቁዋም ስደት ነበር
የነበረኝ አመራጭ፡፡ ወደ ሱዳን ከተሰደድኩ በሁዋላ ለተወሰነ ጊዜ ስራ ለማግኘት ከባድ የነበር ቢሆንም በሁዋላ ላይ ከቻይናዎች ጋር የተያያዘ የመንገድ ስራ ውስጥ ገባው፡፡
ሲኒ ሀይድሮ ፕሮጀክት የሚል መጠሪያ ያለው የአስፓልት ስራ ውስጥ ከአንድ ጉራጌ ጋር ተዋወኩ፡፡ ጃሂል እንዴት መጣራት ይችላል?

ለራሱ ያላወቀበት ሰው እንዴት ሰውን ወደ ሀቅ ያመጣዋል የአምላክ ስራ ነው፡፡ የተዋወኩት ጉራጌ ሙስሊም ነበር፡፡ እና ከሱ ጋር ብዙ ጊዜ የሚያደርገውን እያደረኩ አሳልፍ ነው፡፡ ለእስልምና የነበረው አቁዋም የሚገርም ነበር፡፡ ግን ስለ እስልምና ጥልቅ እውቀት ስለነበረው ወይም ደግሞ ዲኑ በህይወቱ ውስጥ ልውጥ ስላመጣለት አልነበረም፤ግን እንዲሁ ለእስልምና ዘብ መሆን ምርጫው ነበር፡፡ ለእምነቱ
ለዘብተኛ ነገር ነው፡፡ አልኮል መጠጦችን ይጠጣል፡፡ እኔም የዛ ሰአት የመጠጣት ችግር አልነበረኝም፤ምክንያቱም ቄሶች እንኩዋ በመጠጥ ሰክረው በሚያገለግሉበት ቦታ ነው ረዥም እድሜዬን ያሳለፍኩት፡፡

አሊፍ ትዳገደምም ሆነ ትቃና የማያውቅ ጃሂል ነው ለኔ የመጀመሪያው ለውጥ ሰበብ

የሆነኝ…
የጉራጌው እና የኔ ጥል…. ‹‹ ከ2005 አምስት ጀምሮ ነበር ከጉራጌው ሙስሊም ጉዋደኛዬ ጋር ምተዋወቀው፡፡ ታዲያ
በመጨረሻ ወደ ኢትዮጲያ ስንመለስ ሁለታችንም ተዘርፈን ነበር የተመለስነው፡፡ ጥሩ ጉዋደኝነት የፈጠርን እና የተዋደድን ስለነበር ኢትዮጲያ ከመጣን በሁዋላ ተደዋውለን ተገናኘን፡፡ ጉራጌው ጉዋደኛዬ ጋምቤላ ይኖር ስለነበር፤ለኔም ኑሮ ከባድ ስለነበር ወደሱ ለመሄድ ተገደድኩ፡፡ በጣም ይወደኝ ስለነበር ካፊር ነህ
ብሎ ሳይገፋኝም ሚስት እያለሁ አብሬው እንድኖር ፈቅዶልኝ ከሱ ጋር ነበር ቲማቲም ምናምን በረንዳ ተከራይቼ እኖር የነበረው፡፡ ታዲያ አጋጣሚ በቤተክርስቲያን አከባቢ ስናልፍ እኔ ለመሳለም ዝቅ ስል ‹ይሄ

የውሸት እምነት› እኔን ማብሸቁ የተለመደ ነገር ነው፡፡ እኔ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ለቅቄ ብወጣም ለኦርቶዶክስ እምነት የነበረኝ አቁዋም እንደዛው ነበር፡፡
የውሸት እምነት ነው ስል እንዴት እንዲህ ትላለህ
በማለት ከገዛ ጉዋዳኛዬ ጋር እጣላ እና እኩዋረፍ ነበር፡፡ ግን ስላኮረፍኩት እሱ ሀቅን ለኔ ለማሳየት አልሰነፈም፡፡

ስለእስልምና በደንብ ሳይረዳ እኔን ለማስረዳት የሚሞክርበት ሁኔታ የሰነፍ መሆኑን ሲረዳ፤ስለእስልምና የሚያብራሩ ሲዲዎችን፤የአህመድ ዲዳት ዳአዋዎችን አዲስ አበባ ድረስ እየሄደ ያመጣልኝ ነበር፡፡
ግን ለኔ ሀሳቡ የማይገባኝ ነገር ስለነበር ውስጤ ሰርጾ የገባውን የኦርቶዶክስ እምነት ሊፍቅልኝ አልቻለም፡፡ እሱ ለራሱ የወደደውን ለኔ ቢወድልኝም፤መልዕክንትን የመንገር እንጂ በልብ ውስጥ እምነት የመፍጠር አቅም የለውም፡፡…
እምነት የሌለው ጅማሬ…

‹‹ ከአንድ አመት በሁዋላ 2007 ላይ ሌሊት አከባቢ ስለነበር የተኛሁት እንቅልፍ እስከ ረፋድ ቆየሁ፡፡ ጉራጌው ጉዋደኛዬ ስለመስጂድ የነገረኝ ነገር ውስጤ ጥቂት የሆነን ግድ የለሽነትን ፈጠረብኝ፡፡

መስጂድ ውስጥ ምንም የአምልኮ ስርአትን የሚያሳዩ ምስሎች እንደሌሉ እና ከምንጣፍ እና ከግድግዳ
በቀር ሰው ካልሆነ የተለየ ነገር እንደማላይ ነበር የነገረኝ፡፡ ከነገረኝ ቆየት ብሎአል፡፡ ስለክርስትና ጥልቅ እውቀት የሌለው ክርስቲያን መስጂድ ውስጥ መግባትም ሆነ በመስጂድ በኩል ማለፍን እንደሀጥያት
ይቆጥረው ይሆናል፡፡

እኔ ግን ስለክርስትና ጥልቅ እውቀት ነበረኝ፡፡ ምክንያቱም እድሜዬን ሙሉ በሀይማኖታዊ አስተምህሮ ነው ያለፍኩት፡፡ ምንጣፍ እና ግድግዳ የሆነን ቤት ለመጎብኘት መሄድ ለኔ
ብርቅ አልነበረም፡፡ ምንም አይነት ሀይማኖታዊ ተጽእኖም አልነበረውም፡፡ቀኑ የጁመአ ቀን አርብ ነበር፡፡