Get Mystery Box with random crypto!

ትላንት ፖስት ባደረኩት ሠለምቴዎችን በተመለከተ መሠረት ብዙዎቻችሁ ለመልካም ሥራ ያላችሁን ፍላጎት | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ትላንት ፖስት ባደረኩት ሠለምቴዎችን በተመለከተ መሠረት ብዙዎቻችሁ ለመልካም ሥራ ያላችሁን ፍላጎት እና ሠለምቴዎችን ለመርዳት ዝግጁነታችሁን ተረድቻለው ። በጉልበትም በገንዘብም በንዋይ በሃሳብም ከእኛ ጋር ሠለምቴዎችን ለመርዳት ያናገራችሁኝ እህት እና ወንድሞችን አመሰግናለው ። ጀዛኩሙሏህ ኸይር ...! አሏህ በመልካም ሥራ ላይም ጽኑ እና ጠንካራ ለእርሱ ብቻ እና ብቻ ብለን የምንሰራ ያድርገን ።

ወደ እሥልምና የሚገቡ ልጆችን በመርዳት እና በማጠናከር እንዲሁም በአቂዳቸው በኪታቦች በዳዕዋ እጥረት ደካማ የሆኑትን ለማጠንከር እና የአክፍሮት ሃይላትን እየተከላከልን ዳዕዋ እና ኢሥላሚክ ኪታቦች ተደራሽነት እንዲኖር እና በዲናቸው እንዲጠነክሩ የኢታሞች እና የመሳኪኖችን እንባ አባሽ እንደምንሆን በአሏህ ሙሉ ተስፋ አለኝ ።

አላማችን እና እቅዳችን በአሏህ ፈቃድ እና ተወኩል ሰፊ ነውና ከእኛ ጋር መሆን የምትፈልጉ አሁንም በራችን ክፍት ነው ። አናግሩኝ የአህሉል ኸይር ቤተሰብ በመሆን ዲናችንን በጋራ እንካድም እላለው ።

አስሓቡል የሚን የዑማው ብርሃን ..!

https://t.me/+RXYpviFTL70OQdu2