Get Mystery Box with random crypto!

አስ-ሓበል የሚን በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠር አካባቢ ኢስላማዊ (መማሪያ ክፍል | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

አስ-ሓበል የሚን


በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠር አካባቢ ኢስላማዊ (መማሪያ ክፍል) መድረሳን በመገንባት ልጆችን እያስተማረ ይገኛል።

የእስልምና ብርሃን ለሁሉም ይደርስ ዘንድ አሻራውን እያሳረፈ የሚገኘው በአባላቶቹ ጥረት በአላህ እገዛ የኸይር ስራ ጉዞውን ቀጥሏል።

የቲሞችን በመንከባከብ መሳኪኖችን ሠለምቴዎችን በመርዳት የወገኑ ደጀን ለመሆን ሰበብ እያደረሰ የሚገኘው አስ-ሓበል የሚን የአሏህ ፍቃድ ከሆነ ትልቅ መስጂድ የመገንባት እቅድ ይዘናል ።

በብዙ መከራና ስቃይ ውስጥ የሚገኙ ሚስኪኖችን እንባ እያበሰ፤ የበርካታ የቲሞችን እንግልት እየቀነሰ፤ የተቸገሩ ወገኖቹን ችግር ለማቃለል ሰበብ እያደረሰ የሁለት ሀገር ደስታን ለማግኘት እየተጋ የሚገኘው አስ-ሓቡል የሚን ጀመዓ እየሰራቸው የሚገኙትን በርካታ የበጎ ስራ ፕሮጀክቶች ሁሉም ይሳተፍበት ዘንድ እነሆ ጥሪውን አቅርቧል።

በረበና ፍቃድ በአባላቶቹ መልካም ኒያ፤ በኸይር ፈላጊዎች ጥንካሬ፤ ገንዘባቸውን እውቀታቸውን ጊዜአቸውን ሳይሰስቱ በሚደክሙ አባላት እዚህ የደረሰው አስ-ሓቡል የሚን ጀመዓ በርካቶችን በማሳተፍ የኢስላምን ጮራ የዲኑን ብርሃን ለሁሉም ለማዳረስ በርካቶችን አባል ለማድረግ እድሉን አመቻችቷል።

በመሆኑም ጥሪው የደረሳችሁ የአስ-ሓቡል የሚን አባል በመሆን የመልካም ሥራው ተካፋይ እንዲሆኑ እየጋበዝን ለሌሎችም መልእክቱን በማድረስ የኸይሩ ተካፋይ ይሁኑ።።

የአስ-ሓቡል የሚን ቋሚ ቤተሰብ ሲሆኑ በቋሚነት ወርሃዊ ክፍያ በአቅሞ በመሸፈን የመልካም ተግባራት ተሳታፊ ይሁኑ


ኢትዮጵያዊ ውስጥ ነዋሪ ለሆነ 50 ብር

ሳዑድ-አረቢያ እና የመሳሰሉ አረብ ሃገራት ለሚኖሩ 30 ሪያል

በአውሮፓ እና መሰል ሃገራት ለሚኖሩ ወንድምና እህቶች ሲመነዘር ከ50 ( ሃምሳ ) ብር በላይ ሊሆን የሚችል ገንዘብ በየወሩ መነየት ይፈቀዳል።


ለበለጠ መረጃ

+966554225870
+971544106845
+966503917209
+251926142009

በቴሌግራም ¶
https://t.me/joinchat/Th93dNNUa7fV1c79

በዋስት-አፕ ¶
https://chat.whatsapp.com/6O1nFgi4oKHLgB1fdY0Air

አስ-ሓቡል የሚን ከሚሰራቸው የኦላይን ስራም ለምሳሌ ያህል

የሰለምቴዎችን ማራኪ ታሪክ በእንዴት ሰለምኩኝ በተሰኘው ፕሮግራም ያቀርባል ።
ሰለምቴዎችን ከአንደበታቸው ታሪካቸውን ለማድመጥ
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

አስተያየት ለመስጠት ¶
http://t.me//Ashabulyeminbot

አስ-ሓቡል የሚን የዑማው ብርሃን