Get Mystery Box with random crypto!

'የሰለምቴነት ማማር' በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። وَلِلّ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

"የሰለምቴነት ማማር"

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ لِيَجْزِيَ الَّذِينَ أَسَاءُوا بِمَا عَمِلُوا وَيَجْزِيَ الَّذِينَ أَحْسَنُوا بِالْحُسْنَى
53:31 በሰማያት ያለውና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ እነዚያን ያጠፉትን በሠሩት ሊቀጣ እነዚያን "ያሳመሩትንም" በመልካሚቱ (ገነት) ሊመነዳ።

"ያሳመሩትን" ለሚለው የገባው ቃል "አሕሠኑ" أَحْسَنُوا ሲሆን "ኢሕሣን” إِحْسَٰن የሚለው ቃል “አሕሠነ” أَحْسَنَ ማለትም “አስዋበ” “አሳመረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስዋብ” “ማሳመር” ማለት ነው። ለምሳሌ “ሐሠን” حَسَن ማለት “ውብ” “ያማረ” “መልካም” “ጥሩ” “በጎ” ማለት ሲሆን “ሑሥን” حُسْن ማለት ደግሞ “ውበት” “መልካምነት” “ጥሩነት” “በጎነት” ማለት ነው። ኢሕሣን የዲን ማሳመሪያና ማስዋቢያ ነው። ይህን ከተረዳን፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ-2 ሐዲስ ቁ-41
"አባ-ሰዒዲኒል-ኹድሪይ "ረ.ዐ." እንዳስተላለፈው፣ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቼያአለሁ፦ "አንድ የአላህ ባሪያ ከሰለም(እስልምናን ከተቀበለ) እና እስልምናው "ካማረ" "ከተዋበ" *ሙስሊም ከመሆኑ በፊት የሰራውን "ኃጢአት" ሁሉ አላህ ያብስለታል።* ከዚያም(ከአበሰለት) ቡኃላ ቂሷስ(ማመሳሰል) ይሆናል፣ ማመሳሰሉም፦ "በአንድ" መልካም ሥራው *ከአሥር እስከ ሰባት መቶ* እጥፍ ድረስ "ይባዛለታል"። "በአንድ" ኃጢአቱ ደግሞ *መሰሏን* ይመነዳል፣ አላህ ይቅር ብሎ ካላለፈው በስተቀር (ያቺኑ ይመነዳል)።
أَنَّ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ : أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ : " إِذَا أَسْلَمَ الْعَبْدُ فَحَسُنَ إِسْلَامُهُ، يُكَفِّرُ اللَّهُ عَنْهُ كُلَّ سَيِّئَةٍ كَانَ زَلَفَهَا ، وَكَانَ بَعْدَ ذَلِكَ الْقِصَاصُ : الْحَسَنَةُ بِعَشْرِ أَمْثَالِهَا إِلَى سَبْعِمِائَةِ ضِعْفٍ، وَالسَّيِّئَةُ بِمِثْلِهَا إِلَّا أَنْ يَتَجَاوَزَ اللَّهُ عَنْهَا ".

በሐዲሱ መሰረት ማንኛውም ሙስሊም ያልሆነ ሠው "ሁለት" መስፈርቶችን ካሟላ ኃጢኣአቶቹ ሁሉ *እንደሚታበሱለት* ተገልጿል። አንደኛው "ሙሥሊም" መሆን ሲሆን ሁለተኛው "ሙሕሲን" መሆን ነው።

ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ” አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” “መገዛት” “ማምለክ” ማለት ነው
ሙሥሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል ሠለመ” سَلَّمَ “ማለትም “ታዘዘ” “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ታዛዥ” “አምላኪ” ማለት ነው፦
21፥108 ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *“አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን*? በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

ስለዚህ የመጀመሪያ መስፈርት ለአንድ አምላክ ፍፁም መታዘዝን እርሱን በብቸኝነት መገዛት ሲሆን ይህ ደግሞ ከኢሕሳን ጋር የተያያዘ ነው።

“ኢሕሣን” ማለት ደግሞ “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ” "መገዛት" ማለት ነው፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 47 , ሐዲስ 6
…ዑመር ኢብኑ ኸጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው ወደ ነብያችንﷺ በመምጣት እንዲህ በማለት ጠየቃቸው፦ እስኪ ስለ "ኢሕሳን" ንገረኝ፣ እርሳቸውም፦“ኢሕሳን" ማለት አላህን ልክ እንደምታየው አድርገህ ማምለክ፥ አንተ እንኳን ባታየው እርሱ ያይሃልና” አሉ።عن عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ
قَالَ : فَأَخْبِرْنِي عَنِ الْإِحْسَانِ. قَالَ : " أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ "
ስለዚህ አንድ ሠው ለእስልምናው ማማር ዋነኛው ነገር ለአላህ ብሎ ሥራን አጥርቶና አሳምሮ "በኢኽላስ" መስራቱ ነው።

ለአላህ ብሎ ተነይቶ መልካም ሥራዎችን መሥራት "ኢኽላስ" ይባላል፥ “ኢኽላስ” إِخْلَاص የሚለው ቃል “አኽለሰ” أَخْلَصَ‎ ማለትም “አጠራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከወቀሳና ሙገሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ የሚደረግ “ማጥራት” ማለት ነው፦
فَاعْبُدِ اللَّهَ مُخْلِصًا لَّهُ الدِّينَ
39:2 አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ኾነህ ተገዛው፡፡

አንድ ሠው በሰለመ ጊዜ ኃጢአቱ ሁሉ ከእርሱ ይታበሳል፦
قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوا إِن يَنتَهُوا يُغْفَرْ لَهُم مَّا قَدْ سَلَفَ
8:38 ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ "ያለፈውን" (ሥራ) "ምሕረት" ይደረግላቸዋል፡፡

አንድ ሠው ከሰለመ ቡኃላ በኢኽላስ ጥርት ያለ ሥራ ከሰራ አንዷ መልካም ሥራው *ከአሥር እስከ ሰባት መቶ* "እጥፍ" አላህ ያባዛለታል፣ ይህም እንደ ሰውዬው *ኒያው* እና *ኢኽላሱ* ደረጃ ይለያያል፦
مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
6:160 በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ *ዐሥር* ብጤዎችዋ አሉት፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው *ብጤዋን* እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡
مَّثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ كَمَثَلِ حَبَّةٍ أَنبَتَتْ سَبْعَ سَنَابِلَ فِي كُلِّ سُنبُلَةٍ مِّائَةُ حَبَّةٍ ۗ وَاللَّهُ يُضَاعِفُ لِمَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ
2:261 የእነዚያ ገንዘቦቻቸውን በአላህ መንገድ የሚለግሱ ሰዎች (ልግስና) ምሳሌ በየዘለላው ሁሉ "መቶ" ቅንጣት ያለባቸውን "ሰባት" ዘለላዎች እንደ አበቀለች "አንዲት" ቅንጣት ብጤ ነው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) "ያነባብራል"፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡

ይህን የቁርኣን አንቀጽ ከላይ ያሳለፍነው ሐዲስ ያብራራዋል፣ *አንዷ* ቅንጣት በላይዋ ላይ "ሰባት" ዘለላዎች ያበቀሉ ሲሆን እያንዳዱ ዘለላ ደግሞ "መቶ መቶ" ቅንጣቶችን ያበቀሉ ናቸው። 7×100=700 ይሆናል። ይህ ማለት የሚጣፋለት እስከ 700 ብቻ ነው ማለት አይደለም። "አላህም ለሚሻው ሰው (ከዚህ በላይ) *ያነባብራል*፡፡" ባለው መሰረት የሰው ልጅ "ኒያው" እና "ኢኽላሱ" ምንዳውን ያበላልጠዋል። መነሻው ግን 10 እጥፍ ነው።