Get Mystery Box with random crypto!

ሁለት ሠዎች ተመሳሳይ ሥራን ይሰራሉ፣ ነገር ግን ምንዳቸው እጅጉን የተበላለጠ ነው። ይህም በውስጣቸ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ሁለት ሠዎች ተመሳሳይ ሥራን ይሰራሉ፣ ነገር ግን ምንዳቸው እጅጉን የተበላለጠ ነው። ይህም በውስጣቸው ባሰቡት "ኒያህ" እና "በኢኽላሳቸው" ምክንያት ነው፦
ሱነን-ነሠኢይ ሐዲስ ቁጥር 2528
ከአቢ ሁረይራህ "ረ.ዐ." እንደተወራው ፣ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፣ "አንድ" ዲርሃም(የብር ሳንቲም) "መቶ ሺህ" ዲርሃምን በለጠ፡፡ ይህ እንዴት ይሆናል? ተባሉ፣ እርሳቸውም፦ አንድ ግለሰብ "ሁለት" ደራሂም(የብር ሳንቲሞች) ብቻ ነበሩት፣ *አንዷን* ዲርሃም አንስቶ ለገሰ(መፀወተ) ፣ ሌላኛው ግለሰብ ከአካበተው "መቶ ሺህ" ሃብት አንስቶ መፀወተ፡፡ "አሉ"፡፡
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " سَبَقَ دِرْهَمٌ مِائَةَ أَلْفٍ ". قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَكَيْفَ ؟ قَالَ : " رَجُلٌ لَهُ دِرْهَمَانِ ؛ فَأَخَذَ أَحَدَهُمَا فَتَصَدَّقَ بِهِ، وَرَجُلٌ لَهُ مَالٌ كَثِيرٌ، فَأَخَذَ مِنْ عُرْضِ مَالِهِ مِائَةَ أَلْفٍ، فَتَصَدَّقَ بِهَا ". الحديث:حسن

አላህ ዘንድ ተፈላጊነቱ "የሥራ ብዛት" ሳይሆን "የሥራ ጥራት" ነው፡፡ አላህ ለሚሻው ሠው አንዷን መልካም ሥራ ከ700 "እጥፍ" በላይ ያነባብራታል፡፡ ሁለቱም መፀወቱ ግን በምንዳ ተበላለጡ ፣ ያበላለጣቸው "ኒያቸው እና "ኢኽላሳቸው" እንጂ ሌላ አይደለም"፡፡

“ኒያህ” نِيَّة የሚለው ቃል “ነዋ” نَوَى ማለትም “ወጠነ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ውጥን”intention” ማለት ነው። ኒያህ በልብ ውስጥ የሚቀመጥ እና አላህ ብቻ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፦
15፥51 *”አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል*፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي قُلُوبِكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَلِيمًا

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 47
ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ ብለዋል፦ *”ሥራ የሚለካው በውጥን ነው፥ ማንኛውም ሰው የወጠነውን ያገኛል። عَنْ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الأَعْمَالُ بِالنِّيَّةِ، وَلِكُلِّ امْرِئٍ مَا نَوَى،

በመጨረሻም አላህ እንዲህ ይላል፦
ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا
18:110 የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ "መልካም ሥራን ይሥራ"፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡

በጥሩ ሁኔታ ጌታውን መገናኘት የፈለገ "ብዙ ሥራ ይሥራ" ሳይሆን "መልካም ሥራ ይሥራ" በማለት "የኢሕሣንና" "የኢኽላስን" "የኒያን" *ወሳኝነት* እና አስፈላጊነት ይገልፃል፡፡

*የእድሜ* መብዛት የሥራ መብዛትን ሊያስገኝ ይችላል፤ የሥራ መብዛት ግን *የምንዳን* መብዛት "ላያስገኝ" ይችላልና አላህ ሆይ! እስልምናቸው አምሮ ሥራን በጥሩ "ኒያህ፣ "በኢኽላስ፣ "በኢሕሣን፣ ሠርተው አንተን ከሚገናኙት አድርገን! አሚን፡፡

በወንድም መህዲ
http://t.me/AshaBuleyamine