Get Mystery Box with random crypto!

ቃል እያጣሁልሽ ምንም የማልልሽ በአይኖቼ ብቻ በስስት እያየው በዝምታ ውስጥም አዎ ወድሻለው ወድሻ | መፅሐፍት

ቃል እያጣሁልሽ
ምንም የማልልሽ
በአይኖቼ ብቻ በስስት እያየው
በዝምታ ውስጥም አዎ ወድሻለው
ወድሻለው እምቢታሽንም እየሰማው
እሺ የምትል ቃል ከአንደበትሽ
ለመስማት እንኳን መች ተመኘው
ምን ስትይ ከልቤ አፋፍ
አገኘሽኝ ስንከረፈፍ
ወና የሆነው ቤቴ
ምንም የለው እኔነቴ
ወና ኡና ማጀት
ምን ስትይ ፍቅር ዘራሽበት
አውቃለሁ ፍቅር ትርጉሙን አቷል
ፍቅር ፍቅርነትን ትቶ ተራ ቃል ሆኗል
ግን እኔ ፍቅሬ ስልሽ
የዘመኑን ፍቅር ከቶ እንዳይመስልሽ
ልክ ድሮ እንደ ነበረው ፍቅር
ልክ እንደድሮው
በስዕሉ ላይ ያለበት ጦር ተወርውሮ
ልክ እንደዛ እንደድሮ
እወድሻለው