2022-07-15 11:26:56
እሁድ ቀን ከቀረሽ
°°°°°°°°°°°°°
እሁድ ቀን ከቀረሽ ሌላ ቀን አትምጪ ፣
ለኔ ሳምንት የለም ከ እሁድ ሳምንት ውጪ ፣
አንድ ቀን አይደለም ስጠብቅሽ እሁድ ፣
ሳምንትን ያስንቃል አሳየኝ ስንት ጉድ ።
ከሰኞ ተነስተሽ ልክ እስከ ቅዳሜ ፣
ይፈጥናሉ ቀናት ያጥራሉ ከጳጉሜ ፣
ቅዳሜ ካለፈ ለእሁድ እጁን ሰጥቶ ፣፣
ያላገባ አግብቶ ያገባውም ፈቶ ፣
ያለቀሰው ስቆ ፣
የተጣላው ታርቆ ፣
ተሜው ተመርቆ ፣
መፅዋቹ ተነጥቆ ፣
እድር ለቅሶ ሳይቀር ሁሉንም አድርሶ ፣
ደሀ ተለውጦ ያበላል ደግሶ ፣
እሁድ ለዚ ታምር መቼ ቀኑ አንሶ ።
ርዝማኔው ታውቆ የተባለ ሰንበት ፣
ሰንበት ሰንበትበት እሁድ ነው ቀን ማለት ፣
ሰአቱ ቢለካ ሳምንት ሚወጣለት ።
እሁድ ቀን ከቀረሽ ሌላ ቀን አትምጪ ፣
ሌላ ሳምንት የለም ከእሁድ ሳምንት ውጪ ፣
አንድ ቀን አይደለም ስጠብቅሽ እሁድ ፣
ሳምንትን ያስንቃል አሳየኝ ስንት ጉድ ።
ዳጊ
3.0K viewsAviatrices , 08:26