🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አንቺን መሳይ ሙሉ ጎጃም ውብ...የውብ ዳር! የመንፈስ ጣዕም እኔን መሳይ ሰው ቢለምድሽ ብትወደጅ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንቺን መሳይ ሙሉ ጎጃም
ውብ...የውብ ዳር! የመንፈስ ጣዕም
እኔን መሳይ ሰው ቢለምድሽ
ብትወደጅ ብትረቺ አይግረምሽ!
እውነት እውነት እውነት ውዴ፣
ማር ነሽ እኮ ትኩስ እሸት
እምቡጥ ቢጤ ጽጌሬዳ ጣፋጭ ፍጥረት!
ይብላኝ ለኔ...!
ስትርቂኝ ለምባባው እያየሁሽ ለምራብሽ
በናፍቆትሽ ለምከሳው ለምባዝን በትዝታሽ!
በይ አለሜ...!
አምላክ ፈቅዶ አንድ እስክንሆን፣
ድመቂልኝ!  ሰላ በይ
ግና ደግሞ እንዳልፈራ ፣
ብዙ አትራቂኝ በነግ በሰርክ ላይኔ ታይ
እኔ እንደሆን...
ብትንቂኝ ብታከብሪኝ ብትገፊኝም ብታቅፊኝም
በማርያም ስም እምላለሁ ካንቺ ሌላ ሴት አለምድም!

እወድሻለሁ...!!!

(ታደሰ ደምሴ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19