Get Mystery Box with random crypto!

:      ማን ነሽ?? በምን አፈር ቀምሞ ሰራሽ                  ነፍስሽን እንደምን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

:      ማን ነሽ??


በምን አፈር ቀምሞ ሰራሽ
                 ነፍስሽን እንደምን ለካው?
ምሳሌ ከየት አገኘ
               ምን ሲያረግ ይሄን አሰበው?

እኔማ ለራሴ ገዢ
             እል ነበር ሁሉን አውቃለሁ
አዋቂ ጥበበኛ ሰው
            ጀግና ነኝ አንቺን እስካየሁ

ወጣሁኝ ሰልፍ ወደአምላኬ
ስሰፍረው ቢያንስ ልኬ
አንተ ጌታ ሸክላ ሰሪ
            የሷን ፈጥረህ ጌጥ ያረከው
ምነው የኔን
ምነው ልቤን ጀበና አርገህ ከእሳት ጣድከው

ሙግት ያዝኩኝ ከጌታየ ከፈጣሪሽ
ከላይ ነኝ ስል ቢያሳንሰኝ ደጉ ሰሪሽ

እንቆቅልሽ ሆነሽ መጣሽ
በምን አቅሜ ችየ ልርታሽ
እንዳልመልስ ጥበብ አነሰኝ
ሀገር አልሰጥ እትብቴ ያዘኝ

በጥያቄ አጥረሽብኝ
      በየት በኩል ልግባ ቅጥርሽ
በጥበቡ ፈትነሽኝ
       እንዴት ብየ ልቁም ስርሽ

አልከትሽ ነገር ውጬ ሆዴ
በምን ችሎ ሊያቅፍሽ ክንዴ

አልደርብሽ እንደሸማ
ወይ አልረሳሽ እንዳልሰማ

እንዳልስምሽ ከንፈርሽ እሳት
እንዳልተውሽ ቀልቤን ነሳት

ማን ነኝ? ብለሽ ጠይቀሽኝ
               ማን ነሽ ብየ ልመልስሽ?
እኔ እንደሆንኩ ጥበብ የለኝ
                ጥበበኛው እሱ ይሁንሽ!

            ማነሽ?


            በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19