Get Mystery Box with random crypto!

በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ ኮነሌል ገመቹ አያናን ጨምሮ13 ተከሳሾች በነጻ ተሰናበቱ ፡፡ በዛ | @እንደኔ እይታ.....

በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ ኮነሌል ገመቹ አያናን ጨምሮ13 ተከሳሾች በነጻ ተሰናበቱ ፡፡

በዛሬው ቀጠሮ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3 ኛ የፀረሽብር እና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን የሰጠው፡፡
ተከሳሾቹ በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ በተለያዩ አካባቢዎች ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ጋር በመቀናጀት የኦሮሚያ ክልል መንግስትን በሀይል ለማውረድ ፡በተለያዩ ቦታዎች የህብረተሰቡን በማሸበር፡የመንግስት ሰራተኞችን እና የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊሶች ላይ ጥቃት በማድረስ በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡
ይሁንና ፍርድቤቱ አቃቢህግ ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ የወንጀል ህጉን ስለመተላለፋቸው በተገቢው የሚያስረዳ ማስረጃ አላቀረበም ሲል በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን ሰቷል፡፡

Via ታሪክ አዱኛ

@endenaendena