Get Mystery Box with random crypto!

የእርግቢቱ ነገር ነገሩ የሆነው በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ነው። | @እንደኔ እይታ.....

የእርግቢቱ ነገር

ነገሩ የሆነው በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ነው። ጉባኤው በሰዓቱ በአካባቢያዊ የሰላምና የፀጥታ አጀንዳ ላይ ይመክር ይዟል። በመሀል ወደ ጉባኤው አዳራሽ ዘልቃ የገባች አንዲት እርግብ የምክር ቤቱ ታዳሚ በሆኑትና አቶ አለሙ ድንቻ በተባሉት የአገር ሽማግሌ አናት ላይ ለግማሽ ሰዓት ያህል መቀመጧ አግራሞትን ፈጥሯል።

አቶ አለሙ ድንቻ በምክር ቤት ጉባኤ ላይ የተገኘሁት በአባልነት ሳይሆን በወረዳው ነዋሪነቴና በአገር ሽማግሌነት ተጋብዤ ነው ይላሉ። አቶ ዓለሙ በመቀጠልም "እርግቢቱ ወደ አዳራሹ ስትገባ ሁሉም ይመለከታት የነበረ ቢሆንም በሰው አናት ላይ ታርፋለች ብሎ የገመተ አልነበረም። የጉባኤው አባላት ትኩረት ተረጋግታ አናቴ ላይ ወደተቀመጠችው እርግብ በመሆኑ ለደቂቃዎች የጉባኤው ሂደት እንዲቋረጥ ሆኗል። አባላቱ ከመቀመጫቸው በመነሳት በስልኮቻቸው ፎቶ ያነሱኝ ነበር። ከደቂቃዎች በኋላ በምክር ቤት አፈ ጉባኤ ማሳሰቢያነት የተቋረጠው ውይይት ቢቀጥልም እርግቢቱ ግን ለግማሽ ስዓት ያህል በአናቴ ተቀምጣ ከቆየች በኋላ በመጨረሻ አዳራሹን ለቃ ሄዳለች" ብለዋል።

በሁኔታው በእሳቸውም ሆነ በሌሎች የጉባኤው አባላት ላይ ስለፈጠረው ስሜት የተጠየቁት አቶ ዓለሙ "አንዳንዶች ምን መስለሃት ይሆን? በማለት ሲቀልዱብኝ ሌሎች ደግሞ ጉባኤው ሲወያይ ከነበረው የሰላም አጀንዳ ጋር በማገናኘት ከፈጣሪ የተላከች የሰላም ፣ የበረከትና የተስፋ ምልክት አድረገው የቆጠሩም አሉ" ብለዋል።

Via #DW