Get Mystery Box with random crypto!

@እንደኔ እይታ.....

Logo of telegram channel endenaendena — @እንደኔ እይታ.....
Logo of telegram channel endenaendena — @እንደኔ እይታ.....
Channel address: @endenaendena
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 5.02K
Description from channel

የምናያቸውንና የምንሰማቸውን የርዕዮተ አለም፣ፖለቲካ እዲሁም ማህበረሰባዊ እውነታዋች በተጨማሪም
ግጥምና ወግም ከኛ እልፍኝ አይጠፋም
ለ እርሶዎም እናደርሳለን
ለአስተያየቶ @Endenaeytabot ይጠቀሙ
ለሀሳብና አስተያየት ወይም
ተጨማሪ መረጃ ካሎት
👇👇👇👇👇👇
@Endenaeytabot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages

2022-01-18 08:42:44 .....
በመፋለም ብዛት ቀድሞ የታነፀው ስለፈራረሰ
ከልብ ምንጫችን ላይ የሚፈልቀው ኹሉ ስለደፈረሰ
ርቱዕ የነበረ አንደበታችንም ባ'ፍረት ተለጎመ
ከልባችን መዝገብ ድል ማድረግ ተፍቆ መሸነፍ ታተመ
እኽኽኽ ደከመኝ.....
3.4K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 05:42
Open / Comment
2021-06-23 07:19:16 1953 (መንግስቱ ነዋይ ና ገርማሜ ነዋይ ለውጥ ለክሱና ከሸፈ ሰዎች ሞቱ። ነፍ ኪሳራ ደረሰ)

66 (ከአብዮቱ ፍንዳታ ቦኋላ እነ ኢሃፓ ተሟገቱ ለውጥ ለመፍጠር ሞከሩ። ከሸፈ። ነፍ ሰው ሞተ። አገር ከሰረች።)

81 (የደርግ ጀነራሎች ለውጥ ሞከሩ። ከሸፈ። ጀነራሎቹ ሞቱ። ወታደራዊ ውድቀት ሆነ። አገር ከሰረች)

97 (ቅንጅት ለውጥ ሞከረ። ነፍ ወጣት ሞተ። ለውጥ ከሸፈ። አገር ከሰረች።)

ሁሌም እንደምለው የአፍሪካ ፖለቲካ ግም ነውና ራስህን ከእሳቱ ጠብቅ። የወደድከውን ምረጥ። የመረጥከው ባያሸነፍ አራዳ ሁነ ህይወትህን ቀጥል እንጂ ግልፍ አትበል። በፖለቲካ ማእበል እንዳትወስድ። በስሜት እንዳትነዳ። ራስህን ከአደጋ ጠብቅ። (አባታዊ ምክሬ ነው )
@endenaendena
10.2K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 04:19
Open / Comment
2021-06-16 17:02:32
የታጣቂዎች ጥቃት የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ነፍስ ነጠቀ።

በኮንስትራክሽን የስራ ላይ ተሰማርተው በሙያቸው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን እያገለገሉ የነበሩ ሁለት ወጣት ኢንጂነሮች በታጣቂዎች ተገደሉ።

#አሥራት_ሺካ እና #ሮቤል_ልደቱ የተባሉት ወጣት ኢንጂነሮች ትላንት ሰኔ 8/2013 ለሥራ ጉዳይ "አማሮ ልዩ ወረዳ" ሲጓዙ "ጀሎ" በምትባል ቀበሌ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው አልፏል።

ሁለቱም ወጣት ኢንጂነሮች ባላቸው እውቀት ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ነው በታጣቂዎች በግፍ የተገደሉት።

የወጣቶቹን ግድያ የአማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያረጋገጠ ሲሆን ጉዳዩን ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቀናል ብሏል።

በሌላ በኩል የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽን ባለልስጣን ባወጣው የሀዘን መግለጫ ወጣት ሮቤል ልደቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንግስት ፕሮጀክቶች ግንባታ ጥራት ክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሂደት ባለሞያ እንደነበር ገልጾ በህልፈቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።


የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ስለግድያው ፣ ጥቃት ፈፃሚዎቹ ስለመያዛቸው እና ሌሎች ተያያዥ መረጃ እንዲሰጠን ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
8.7K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, edited  14:02
Open / Comment
2021-06-16 17:02:32
5.4K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 14:02
Open / Comment
2021-06-16 17:02:32
4.8K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 14:02
Open / Comment
2021-06-16 17:02:31
4.3K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 14:02
Open / Comment
2021-06-11 08:33:04
እነ እስክንድር ነጋን በዕጩነት ለመመዝገብ 1.3 ሚሊዮን የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ተቃጠሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮልና ወ/ሮ ቀለብ ሥዩምን በዕጩነት በመመዝገቡ ለሚወዳደሩባቸው ቦታዎች ቀደም ሲል አሳትሟቸው የነበሩት 1.3 ሚሊዮን የድምፅ መስጫ ወረቀቶች እንዲቃጠሉ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ለፍርድ ቤት አስታውቋል። 

Via Reporter
4.9K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 05:33
Open / Comment
2021-06-11 08:29:18
“ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን እናደርጋለን”- ኢዜማ

“ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን” ለማድረግ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አስታወቀ፡፡

ኢዜማ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን አቋም በተመለከተ ህዝባዊ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ “ኢትዮጵያ የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ ናት” ያሉት የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለሀገር በሚጠቅሙ ጉዳዮች ከአብንም፣ ከባልደራስም፣ ከብልጽግና ጋር እንሰራለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕ/ር ብርሃኑ በከተማዋ ላይ ካለው የልዩ ጥቅም ጥያቄ ጋር በተያያዘ “ለአንድ ዘር/ብሔር የሚሰጥ የተለየ ጥቅም የሚባል ነገር የለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ ልትሰፋ እና ልታድግ እንደሚገባ የተናገሩም ሲሆን “በዙሪያዋ ያሉት አርሶ አደሮችም መጠቀም አለባቸው” ብለዋል።

ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ “በአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ አንደራደርም ” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፤ መሐል ላይ አርማ ካስፈለገ በሕዝብ ምርጫና በመነጋገር ብቻ ምላሽ ሊሆን እንደሚችል በማከል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተዘወተረ የመጣውን የከተማ አስተዳደሩን የምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመት አሰራር ተችተዋል፡፡

“በምክትል ከንቲባ ማዕረግ እየተባለ፣ የሕዝብ ውክልና የሌለው ሰው የሚሾምበት አሰራር ትክክል አይደለም” ሲሉም ነው ያስቀመጡት፡፡

ከብልጽግና ጋር የተደረገ ውህደት እንደሌለ እና መሠረታዊ ልዩነቶች እንዳሏቸውም ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ካውሰር እድሪስ “ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን እናደርጋለን፤ የሃይማኖት አባቶች እንዲያወግዙትም እንጠይቃለን” ሲሉ ተናግረዋል በመድረኩ፡፡

አል አይን አማረኛ
4.7K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 05:29
Open / Comment
2021-06-05 21:41:27
ኢዜማ በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ ላይ “የማመቻመች አቋም” እንደሌለው አስታወቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ላይ “ምንም አይነት ብዥታ” እንደሌለው እና በጉዳዩ ላይም “የማመቻመች አቋም” እንደማይከተል አስታወቀ።

ፓርቲው ይህን አቋሙን የገለጸው፤ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 28 በአዲስ አበባው ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በነበረው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

የፓርቲውን መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው ዕጩዎች በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማን፣ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው የሚያራምዳቸውን አቋሞች እና አስተሳሰቦች የተመለከቱ ጥያቄዎች ከታዳሚዎች ተነስተዋል።

ሶስት መቶ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የከተማይቱ የባለቤትነት እና የልዩ ጥቅምን የተመለከቱ ጉዳዮች እና ራስን በራስ ማስተዳደርን የተመለከቱ ጥያቄዎች ለፓርቲው ዕጩዎች ቀርበዋል።

ሌሎች ክልሎች በአዲስ አበባ ላይ ያላቸውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ፤ የኢዜማ መሪ በሰጡት ምላሽ “ለአንድ ብሄር የሚሰጥ ልዩ ጥቅም አይኖርም” ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አስታውቀዋል።

ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ደግሞ “አዲስ አበባ መስፋት እስካለባት መስፋት ትችላለች” ብለዋል።

ነገር ግን ይህ የከተማዋ መስፋፋት በዙሪያዋ ያሉ ነዋሪዎችን በሚጠቅም እና በማይጎዳ መልኩ መሆን እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2021/3470/
4.2K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 18:41
Open / Comment
2021-06-05 05:55:33
ሀሳብ አልባ ወንበሮች
---------------------------

በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ብልጽግና ከሀሳብ ክርክር ሲሸሽ የመጀመሪያው አይደለም። "እመጣለሁ" ብሎ ይቀራል። "ቀኑ ይቀየርልኝ" ብሎ ቀኑ ተቀይሮለት ይቀራል። ታዛቢዎች እና ባለሙያዎች በሚታደሙበት "አልከራከርም" ይላል፣ በቀጥታ ስርጭት በሚተላለፍ ክርክር ለመሳተፍ አሻፈረኝ ይላል። ለእኔ ከሌሎቹ ተጨማሪ ሰአት ይጨመርልኝ፣ ሌሎቹ አንድ አንድ አባል ሲወክሉ እኔ ብቻ ሁለት ተከራካሪ ይፈቀድልኝ ብሎ ችክ ይላል... ሰበቡ ማለቂያ የለውም።

ዛሬ ኢቲቪ (EBC) አምስት ፓርቲዎችን በመጋበዝ በባህል እና ቱሪዝም ላይ የምርጫ ክርክር ለማድረግ ቀጠሮ ነበረን። አራት ፓርቲዎች (ኢዜማ፣ እናት፣ አብን፣ ነጻነት እና እኩልነት) በቀጠሮአችን ሰአት ኢቲቪ ስቱዲዮ ተገኝተን ነበር። እኔ እና ዶ/ር ሙሉዓለም ኤዜማን ወክለን ቀድመን ተገኘን። ሀሳብ አልባው ብልጽግና ፓርቲ ግን ቢጠበቅ ቢጠበቅ የውኃ ሽታ ሆነ።

የአራቱ ፓርቲዎች ተወካዮች ይህ የብልጽግና ተደጋጋሚ ነውር ተቀባይነት እንደሌለው እና ብልጽግና ቀረ ተብሎ ክርክሩ ከሚሰረዝ የመጣነው ፓርቲዎች ክርክራችንን መቀጠል አለብን የሚል አቋም ያዝን። ኢቲቪ ግን ጌቶቹን በመፍራት "ክርክሩ አይካሄድም" አለ።

ከአንድ ሰአት በላይ ተጨቃጭቀን ኢቲቪ ሀሳቡን እንደማይቀይር ስንረዳ ከኢዜማ የተወከልነው እኔ እና ዶ/ር ሙሉዓለም ለመጡት ፓርቲዎች አንድ ሀሳብ አቀረብን። "ስቱዲዮ ውስጥ ገብተን በየቦታችን እንቀመጥ የብልጽግና ወንበሮች ለታሪክ ባዶ ሆነው ፎቶ እንነሳ" አልን። ፓርቲዎቹ ተስማሙ። እነሆ ይህንን ፎቶ በስልካችን ካሜራ ለታሪክ አስቀረን።

ደራሲ በዓሉ ግርማ "ከአድር ባይ ብዕር ይልቅ ባዶ ወረቀት ብዙ ይናገራል" እንዲል እኔ ደግሞ "ከሆድ አደር ካድሬ ይልቅ ባዶ ወንበሮች ሀሳብ አላቸው" እላለሁ።
3.8K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 02:55
Open / Comment