Get Mystery Box with random crypto!

የታጣቂዎች ጥቃት የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ነፍስ ነጠቀ። በኮንስትራክሽን የስራ ላይ ተሰማርተው | @እንደኔ እይታ.....

የታጣቂዎች ጥቃት የሁለት ወጣት ኢንጂነሮችን ነፍስ ነጠቀ።

በኮንስትራክሽን የስራ ላይ ተሰማርተው በሙያቸው ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን እያገለገሉ የነበሩ ሁለት ወጣት ኢንጂነሮች በታጣቂዎች ተገደሉ።

#አሥራት_ሺካ እና #ሮቤል_ልደቱ የተባሉት ወጣት ኢንጂነሮች ትላንት ሰኔ 8/2013 ለሥራ ጉዳይ "አማሮ ልዩ ወረዳ" ሲጓዙ "ጀሎ" በምትባል ቀበሌ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው አልፏል።

ሁለቱም ወጣት ኢንጂነሮች ባላቸው እውቀት ህዝባቸውን እና ሀገራቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ነው በታጣቂዎች በግፍ የተገደሉት።

የወጣቶቹን ግድያ የአማሮ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያረጋገጠ ሲሆን ጉዳዩን ለደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቀናል ብሏል።

በሌላ በኩል የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽን ባለልስጣን ባወጣው የሀዘን መግለጫ ወጣት ሮቤል ልደቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመንግስት ፕሮጀክቶች ግንባታ ጥራት ክትትል እና ቁጥጥር ስራ ሂደት ባለሞያ እንደነበር ገልጾ በህልፈቱ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።


የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ስለግድያው ፣ ጥቃት ፈፃሚዎቹ ስለመያዛቸው እና ሌሎች ተያያዥ መረጃ እንዲሰጠን ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።