Get Mystery Box with random crypto!

@እንደኔ እይታ.....

Logo of telegram channel endenaendena — @እንደኔ እይታ.....
Logo of telegram channel endenaendena — @እንደኔ እይታ.....
Channel address: @endenaendena
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 5.02K
Description from channel

የምናያቸውንና የምንሰማቸውን የርዕዮተ አለም፣ፖለቲካ እዲሁም ማህበረሰባዊ እውነታዋች በተጨማሪም
ግጥምና ወግም ከኛ እልፍኝ አይጠፋም
ለ እርሶዎም እናደርሳለን
ለአስተያየቶ @Endenaeytabot ይጠቀሙ
ለሀሳብና አስተያየት ወይም
ተጨማሪ መረጃ ካሎት
👇👇👇👇👇👇
@Endenaeytabot

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages 2

2021-06-01 21:39:51
#UPDATE

#ፍትህ_ለፌቨን!

ግድያ የተፈፀመው እዚሁ ሀዋሳ ነው።

ኃይሌ ሪዞርት አካባቢ አሳ መሸጫ ማህበር እንዳጣራሁት መረጃ ግለሰቡ በተደጋጋሚ ሴቶችን በጀልባ ላዝናናሽ በማለት ወደ ውስጥ አርቆ ይዞ በመሄድ ሰው መድረስ የማይችልበትና ጮኸው እንኳ እንደማያመልጡ የሚያውቁበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ለፆታዊ ትንኮሳ ጥያቄና ከዚያ ከፍ ሲልም ወደ ማስገደድ ይመጣል።

የግለሰቡን ማስፈራራት እና፣ ጮኸው እንኳ ሰው የማይደርስበት ቦታ ላይ እንዳሉ ሲያውቁ ያሎት አማራጭ ከግለሰቡ የሚቀርብልዎትን ክፉ ሀሳብ መቀበል አለበለዚያም ዘሎ ሀይቅ ውስጥ መግባት ሊሆን ነው።

ይህች ታዳጊ ግን ይህ ዕጣ ደርሷታል! ሞትን ፈርተው በግድ ወንጀል ተፈፅሞባቸው ምንም እንዳልተፈጠረ የሄዱ እህቶችን ቤት ይቁጠራቸው።

የሀዋሳ ከተማ ወንጀል ክትትልና ምርመራ ይህንን ጉዳይ አጣርቶ ተገቢውን የህግ ቅጣት ወንጀል ፈፃሚውን እንዲቀጣ ስል ድምፄን አሰማለሁ።

በታዳጊዋ አሰቃቂ ሞት ሀዘን ለደረሰባችሁ ቤተሰቦችና ጓደኘኞቿ በሙሉ መፅናናትን እመኛለሁ!!

Via #EFREM
3.9K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 18:39
Open / Comment
2021-06-01 14:53:09
3.3K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 11:53
Open / Comment
2021-06-01 11:00:55
ወጣ የተባለውን የድምፅ ፋይል ሰማሁት!

ለትንሽ ደቂቃዎች አንዳንድ ኦንላይን የሚገኙ ፋይሎችን ለማየት ሞክሬ እነዚህን አገኘሁ፣ በስርዐት ቁጭ ተብሎ ቢፈልግ ሌሎቹም ሊገኙ ይችላሉ። ብዙ ሰው ስለጠየቀኝ ይህን ላጋራችሁ ወደድኩ፣ ለማንኛውም የራሳችሁን ግንዛቤ ውሰዱ፣ መረጃው ይኸው:

"ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ያስቸግራል"
https://fb.watch/5R4XnZZhLT/ (ደቂቃ 19:17)

"ምንም ጥርጣሬም፣ ሚስጥርም የለውም"
https://www.facebook.com/101014104879842/videos/486715285867675 (ደቂቃ 25:26)

"የኛ ካድሬዎች..."
https://www.facebook.com/101014104879842/videos/486715285867675 (ደቂቃ 15:02)

"ትናንሽ የሚባል ስህተት፣ ትናንሽ የሚባል ጥፋት ማረም መቻል አለብን"


(ደቂቃ 2:52)

"ካለፍንባቸው ፈተናዎች አንፃር ይህን ማሳካት ብዙ ከባድ አይደለም"


(ደቂቃ 3:25)

"ምርጫውን አጨናግፈን..."
https://fb.watch/5RvjGNvoCf/ (ደቂቃ 0:06)

መልካም ቀን!
EliasMeseret
3.3K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 08:00
Open / Comment
2021-06-01 10:47:31
ሃገራት በገንዘብ ተሽጠዋል

የሆነ ቀን በሀገራችን ሳይቀር በስማቸው ጎዳና የተሰየመላቸው የቀድሞው የእንግሊዝ ጠ/ሚ ሰር ዊንስተን ቸርችል ለ ቃለ-መጠየቅ ወደ ቢቢሲ ቢሮ በታክሲ በመሄድ ላይ ነበሩ።

እዛ እንደደርሱ ሹፌሩን እስክመለስ ድረስ እባክህ ለአርባ ደቂቃ እንዲጠብቃቸው ጠየቅኩት። ሾፌሩ ግን "ይቅርታ አልችልም ምክንያቱም የዊንስተን ቸርችልን ኢንተርቪው ለማዳመጥ ወደ ቤት መሄድ ይኖርብኛል" ሲል መለሰላቸው።

ንግግራቸውን ለማዳመጥ ባሳየው ፍላጎት ተደንቀው ደስ አላቸው። ማንነታቸውንም ሳይነግሩት ለታክሲ ሾፌሩ አስር ፓውንድ አውጥተው ሰጡት።

ሾፌሩ ገንዘቡን እንደተቀበለ ሃሳቡን ቀየረ!*
"ጌታዬ እንዲያውም እስኪመለሱ ድረስ ለሰዓታትም ቢሆን እጠብቆታለሁ፣ ቸርችል ወደ ገሃነም ይግባ!" ብሏቸው አረፈ!

"ገንዘብ ግለሰባዊ እና ገዥ የሚባሉ መርሆዎቻችንን እንዴት እነደሚያስቀይር ተመልከቱ! ሃገራት በገንዘብ ተሽጠዋል ክብር በገንዘብ ተቀይሯል። ቤተሰብ በገንዘብ ተብትኗል፣ጓደኛሞች ለገንዘብ ሲሉ ተለያይተዋል።"

የሰው ነብስ ለገንዘብ ሲል እንዲሁ መና ቀርቷል። በጥቅሉ ሰዎች ለገንዘብ ሲሉ ያደሩ ባሮች ሆነዋል!! “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና !!!”

ጌታ ሆይ ይሄንን ብቻ አሳልፈኝ !
#Eyasu Tesema Meeried
3.1K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 07:47
Open / Comment
2021-05-17 15:10:55
የእርግቢቱ ነገር

ነገሩ የሆነው በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ወናጎ ወረዳ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ነው። ጉባኤው በሰዓቱ በአካባቢያዊ የሰላምና የፀጥታ አጀንዳ ላይ ይመክር ይዟል። በመሀል ወደ ጉባኤው አዳራሽ ዘልቃ የገባች አንዲት እርግብ የምክር ቤቱ ታዳሚ በሆኑትና አቶ አለሙ ድንቻ በተባሉት የአገር ሽማግሌ አናት ላይ ለግማሽ ሰዓት ያህል መቀመጧ አግራሞትን ፈጥሯል።

አቶ አለሙ ድንቻ በምክር ቤት ጉባኤ ላይ የተገኘሁት በአባልነት ሳይሆን በወረዳው ነዋሪነቴና በአገር ሽማግሌነት ተጋብዤ ነው ይላሉ። አቶ ዓለሙ በመቀጠልም "እርግቢቱ ወደ አዳራሹ ስትገባ ሁሉም ይመለከታት የነበረ ቢሆንም በሰው አናት ላይ ታርፋለች ብሎ የገመተ አልነበረም። የጉባኤው አባላት ትኩረት ተረጋግታ አናቴ ላይ ወደተቀመጠችው እርግብ በመሆኑ ለደቂቃዎች የጉባኤው ሂደት እንዲቋረጥ ሆኗል። አባላቱ ከመቀመጫቸው በመነሳት በስልኮቻቸው ፎቶ ያነሱኝ ነበር። ከደቂቃዎች በኋላ በምክር ቤት አፈ ጉባኤ ማሳሰቢያነት የተቋረጠው ውይይት ቢቀጥልም እርግቢቱ ግን ለግማሽ ስዓት ያህል በአናቴ ተቀምጣ ከቆየች በኋላ በመጨረሻ አዳራሹን ለቃ ሄዳለች" ብለዋል።

በሁኔታው በእሳቸውም ሆነ በሌሎች የጉባኤው አባላት ላይ ስለፈጠረው ስሜት የተጠየቁት አቶ ዓለሙ "አንዳንዶች ምን መስለሃት ይሆን? በማለት ሲቀልዱብኝ ሌሎች ደግሞ ጉባኤው ሲወያይ ከነበረው የሰላም አጀንዳ ጋር በማገናኘት ከፈጣሪ የተላከች የሰላም ፣ የበረከትና የተስፋ ምልክት አድረገው የቆጠሩም አሉ" ብለዋል።

Via #DW
4.1K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 12:10
Open / Comment
2021-05-17 15:07:15 በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ ኮነሌል ገመቹ አያናን ጨምሮ13 ተከሳሾች በነጻ ተሰናበቱ ፡፡

በዛሬው ቀጠሮ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3 ኛ የፀረሽብር እና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን የሰጠው፡፡
ተከሳሾቹ በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ በተለያዩ አካባቢዎች ከኦነግ ሸኔ አመራሮች ጋር በመቀናጀት የኦሮሚያ ክልል መንግስትን በሀይል ለማውረድ ፡በተለያዩ ቦታዎች የህብረተሰቡን በማሸበር፡የመንግስት ሰራተኞችን እና የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ፖሊሶች ላይ ጥቃት በማድረስ በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ይታወሳል፡፡
ይሁንና ፍርድቤቱ አቃቢህግ ያቀረበው የሰውና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ የወንጀል ህጉን ስለመተላለፋቸው በተገቢው የሚያስረዳ ማስረጃ አላቀረበም ሲል በነጻ እንዲሰናበቱ ብይን ሰቷል፡፡

Via ታሪክ አዱኛ

@endenaendena
3.3K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 12:07
Open / Comment
2021-05-17 15:04:53
በአዲስ አበባ ከ ሀያ ሺ በላይ ንግድ ፍቃዶች ትርፍ በማጣታቸው ፍቃዳቸውን መልሰዋል።

በአንድ አመት ውስጥ ብቻ በአዲስ አበባ የቤት ኪራይና ግብር እንዲሁም ከኮሮናቫይስ እና በሀገሪቱ የተረጋጋ ሰላም አለመኖር ገበያቸውን ያቀዘቀዘው 20 ,679 ንግድ ፍቃዶች ስራቸው ትራፋማ ስላልሆነ ንግድ ፍቃዳቸውን በየክፈለከተማው ለሚገኙ ንግድ ቢሮዎች መመለሳቸውን ፊደል ፖስት የደረሰው መረጃ ያሳያል።
ባለፈው የበጀት አመት 20, 627 ንግድ ፍቃዶች መመለሳቸው ይታወሳል።

በሌላ ጎኑ ደግሞ በዘንድሮ የበጀት አመት 25,188 አዲስ ንግድ ፍቃዶች ተመዝገበዋል።
3.2K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 12:04
Open / Comment
2021-05-13 07:46:39 EID MUBARAK
3.5K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 04:46
Open / Comment
2021-05-11 20:03:25 የዒድ አል-ፈጥር በዓል ሀሙስ ይከበራል!

በዛሬው ዕለት አዲስ የሸዋል ጨረቃ ሊታይ ባለመቻሉ የዘንድሮው ዒድ አል-ፊጥር የሚውለው ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 5 ቀን 2013 መሆኑ መረጋገጡን HARMAIN SHARIFAIN ዋቢ በማድረግ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።

[ዳጉ_ጆርናል]
@endenaendena
3.9K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 17:03
Open / Comment
2021-05-10 21:45:34
“ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” ነገ ግንቦት 03/2013 በመስቀል አደባባይ በደማቅ ሁኔታ እንደሚካሄድ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሀላል ፕሮሞሽን እና ነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት ገለፁ።

ሀሩን ሚድያ
@endenaendena
4.1K views––––•(-• xyxyxy•-)•––––, 18:45
Open / Comment