Get Mystery Box with random crypto!

ሃገራት በገንዘብ ተሽጠዋል የሆነ ቀን በሀገራችን ሳይቀር በስማቸው ጎዳና የተሰየመላቸው የቀድሞ | @እንደኔ እይታ.....

ሃገራት በገንዘብ ተሽጠዋል

የሆነ ቀን በሀገራችን ሳይቀር በስማቸው ጎዳና የተሰየመላቸው የቀድሞው የእንግሊዝ ጠ/ሚ ሰር ዊንስተን ቸርችል ለ ቃለ-መጠየቅ ወደ ቢቢሲ ቢሮ በታክሲ በመሄድ ላይ ነበሩ።

እዛ እንደደርሱ ሹፌሩን እስክመለስ ድረስ እባክህ ለአርባ ደቂቃ እንዲጠብቃቸው ጠየቅኩት። ሾፌሩ ግን "ይቅርታ አልችልም ምክንያቱም የዊንስተን ቸርችልን ኢንተርቪው ለማዳመጥ ወደ ቤት መሄድ ይኖርብኛል" ሲል መለሰላቸው።

ንግግራቸውን ለማዳመጥ ባሳየው ፍላጎት ተደንቀው ደስ አላቸው። ማንነታቸውንም ሳይነግሩት ለታክሲ ሾፌሩ አስር ፓውንድ አውጥተው ሰጡት።

ሾፌሩ ገንዘቡን እንደተቀበለ ሃሳቡን ቀየረ!*
"ጌታዬ እንዲያውም እስኪመለሱ ድረስ ለሰዓታትም ቢሆን እጠብቆታለሁ፣ ቸርችል ወደ ገሃነም ይግባ!" ብሏቸው አረፈ!

"ገንዘብ ግለሰባዊ እና ገዥ የሚባሉ መርሆዎቻችንን እንዴት እነደሚያስቀይር ተመልከቱ! ሃገራት በገንዘብ ተሽጠዋል ክብር በገንዘብ ተቀይሯል። ቤተሰብ በገንዘብ ተብትኗል፣ጓደኛሞች ለገንዘብ ሲሉ ተለያይተዋል።"

የሰው ነብስ ለገንዘብ ሲል እንዲሁ መና ቀርቷል። በጥቅሉ ሰዎች ለገንዘብ ሲሉ ያደሩ ባሮች ሆነዋል!! “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና !!!”

ጌታ ሆይ ይሄንን ብቻ አሳልፈኝ !
#Eyasu Tesema Meeried