Get Mystery Box with random crypto!

“ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን እናደርጋለን”- ኢዜማ “ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል | @እንደኔ እይታ.....

“ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን እናደርጋለን”- ኢዜማ

“ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን” ለማድረግ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አስታወቀ፡፡

ኢዜማ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን አቋም በተመለከተ ህዝባዊ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይቱ “ኢትዮጵያ የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ውስጥ ናት” ያሉት የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለሀገር በሚጠቅሙ ጉዳዮች ከአብንም፣ ከባልደራስም፣ ከብልጽግና ጋር እንሰራለን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕ/ር ብርሃኑ በከተማዋ ላይ ካለው የልዩ ጥቅም ጥያቄ ጋር በተያያዘ “ለአንድ ዘር/ብሔር የሚሰጥ የተለየ ጥቅም የሚባል ነገር የለም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ ልትሰፋ እና ልታድግ እንደሚገባ የተናገሩም ሲሆን “በዙሪያዋ ያሉት አርሶ አደሮችም መጠቀም አለባቸው” ብለዋል።

ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ “በአረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ አንደራደርም ” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፤ መሐል ላይ አርማ ካስፈለገ በሕዝብ ምርጫና በመነጋገር ብቻ ምላሽ ሊሆን እንደሚችል በማከል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተዘወተረ የመጣውን የከተማ አስተዳደሩን የምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመት አሰራር ተችተዋል፡፡

“በምክትል ከንቲባ ማዕረግ እየተባለ፣ የሕዝብ ውክልና የሌለው ሰው የሚሾምበት አሰራር ትክክል አይደለም” ሲሉም ነው ያስቀመጡት፡፡

ከብልጽግና ጋር የተደረገ ውህደት እንደሌለ እና መሠረታዊ ልዩነቶች እንዳሏቸውም ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ካውሰር እድሪስ “ሙስና በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል እንዲሆን እናደርጋለን፤ የሃይማኖት አባቶች እንዲያወግዙትም እንጠይቃለን” ሲሉ ተናግረዋል በመድረኩ፡፡

አል አይን አማረኛ