Get Mystery Box with random crypto!

#እግዚአብሔር_መፍራት_ይገባናል እግዚአብሔር ሊፈራ የሚገባው ታላቅ አምላክ ነው። በመፅሐፍ '' እነ | 🙌 Blëss thë lørd 🙌

#እግዚአብሔር_መፍራት_ይገባናል
እግዚአብሔር ሊፈራ የሚገባው ታላቅ አምላክ ነው።
በመፅሐፍ "" እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ እነሆ፥ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 40:15)።እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ትልቅ ነው።ስለ እግዚአብሔር ታላቅነተ ስንመለከት ግን ሕዝብ ሁሉ በአንድ ላይ በፊቱ እንደ ጠብታ ናቸው።እግዚአብሔር
ልንገልጸው ከምንችለው በላይ ታላቅ ነው።እግዝአብሔር
ከመረዳታችን በላይ ታላቅ ነው።እግዚአብሔር ሰማይ የማይችለው ምድር የእግሩ መረገጫ የሆነ አምላክ ነው።
" እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 66:1)።
በምድር ላይ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ትንሽ ትቢያ ነው።ሕዝብ ሁሉ በፊቱ እንደ ጠብታ ከሆነ እግዚአብሔር ምን ያህል ታላቅ ነው?የእግዚአብሔር አሳብ ከሰው አሳብ
እጅግ ይርቃል።ሰማይ እንደሚርቅ እንዲሁ የእግዚአብሔር አሳብ፣የእግዚአብሔር ማስተዋል ፣የእግዚአብሔር ጥበብ ከሰው አሳብ ይርቃል።ስለሆነም ምንም እንኳ ልጆቹ ብንሆንም ይህንን እግዝአብሔር ልንፈራው ልናከብረው ፤በፊቱም ልንንቀጠቀጥ ይገባናል።
@mezmur_lyrics_channel
@mezmur_lyrics_channel
@mezmur_lyrics_channel