Get Mystery Box with random crypto!

ጋዜጠኛ፦ ለአንድ ሳምንት ዘሚ ስልኳን አጠፋፍታ ጥፍት ብትል በጉዳዩ ላይ ያገባኛል የሚልና የሚከራከ | ቅኔ ያለው ትውልድ

ጋዜጠኛ፦ ለአንድ ሳምንት ዘሚ ስልኳን አጠፋፍታ ጥፍት ብትል በጉዳዩ ላይ ያገባኛል የሚልና የሚከራከር ሰው አለ ይሆን ?


ዘሚ ፦ "አለ ብዬ አስባለሁ ፣ ይኖራል ። ይሄን ያህል የሚጮኹ ባይሆንም። አሁንኮ ስብሰባ ላይ ሌላ ነገር ልናገር እጄን ሳነሳ ኦቲዝም ልትል ነው ሲሉ ሰምቻለው ፤ ኦቲዝሟ ሴትዮ ይሉኛል። "አየሃት ያቺ ሴትዮ አወቅካት ?" ሲባል ፤ ኦቲዝሟ የሚሉም አሉ።

እኔ ባልኖር የሚናገር የለም ሳይሆን የሚያሳዝነኝ የሰዎች ተስፋ አጠፋለሁ ብዬ አዝናለሁ። መኖር የምፈልገው አንድም ለልጄ ነው ፤ በዛም ላይ ለእነዚህ ልጆችና እናቶች ነው። ምክንያቱም ፊቴ እንኳን ትንሽ ከተከፋ እንዴች እንደሚደነግጡ። ተስፋቸው ሆኜ ስለሚያዩኝ ይደነግጣሉ ፣ ይፈራሉ። አንዴ ታምሜ ነበር ያኔ እንዴች እደሆነ መናገር ይቸግራል። ተስፋቸውን አጨልምባቸው ይሆን ብዬ እሰጋለሁ። ፈጣሪንም አትውሰደኝ እስኪስተካከል ፤ ይህን ቤት እስክሠራ ድረስ እለዋለው።". . . . በአንድ ወቅት ከሰጠችው ቃለ መጠይቅ ውስጥ የወሰድኳት ነው . .


# አትውሰደኝ አለችው ፣ ወሰዳት . . ምን አልባት ጭወቷን እንድንሰማው ይሆናል . . . ምን መፃፍ እዳለብኝ አላውቅም እኔ እራሴ. .……ለብላቢ ሃዘን ነው !! ዋርካው ተነስቶ ጠራራ ፀሃይ ሲያቃጥል ተሰምቶኛል…… ብቻዋን አልሄደችም ፣ ብዙ ሸፋኝ የብዙ እናት ነች. . . ልል ምፈልገው . . አንድ ብርም ቢሆን እንኳን ያለን ይሄ ማዕከል እንዲሰራ የበኩላችንን እናርግ ነው. . . ስለነበረች ያልቃል ብዬ እርግጠኛ ነበርኩ ሚጎድል አይመስለኝም ነበር . . አሁን ግን …………

…………እና ያለንን እንስጥ . . .. . ለመስጠት ሚሊየን ማገላበጥ አይጠበቅም መመረጥ ብቻ ነው ሚያስፈልገው . . . የተመረጥን እንሁን !!!


በብዙዋን ነፍስ ውስጥ ትኖርያለች የኔ ልባም ሴት ፣ ከቀይ እንቁ በላይ የሆንሽው ዘሚዬ !!



@keney_serezoch