2020-08-30 22:55:36
ልጅቷ የቤታቸው በር ይንኳኳና ስትከፍተው ቦይፍሬንዷ ነው
ግን አባትዋ በቅርብ ርቀት ሰለነበሩ በስነ-ስርአት ሰላም አላለችውም
ወዲያውኑም ልጁ እንዳይቀባጥር በኮድ
እሷ፦ሀይ ሰላም ነው "አባቴ እቤት ነው" የሚለውን የበውቀቱ ስዩም መፅሀፍህን ልትወስድ መጥተህ ነው?
.
ልጁ፦ወዲያውኑ ነቄ ይልና እር እኔስ
የበአሉ ግርማን
"ታዲያ የት ልጠብቅሽ" የሚለውን መፅሀፍ ልወስድ ነበር።
.
እሷ፦ውይ እሱን መጽሀፍ እንኳን ቶሎ አላገኘውም ባይሆን ያአዳም ርታን "ከማንጎው ዛፍ ጥላ ስር" የሚለውን ልስጥህ
.
ልጁ፦ጥሩ በዛው"እንደ ደርስኩ እደውላለሁ" የሚለውን መጽሀፍም እንዳትርሽው.
.
እሷ፦እር ምንም ችግር የለም
የይስማክ ወርቁን "ቶሎ መጣለሁ ጠብቀኝ" የሚለውንም ይዥልህ መጣለሁ:............
ልጅቷ በሩን እንደዘጋች አባቷ አስቆማትና
አባት፦ በጣም የሚገርም ነው ይህንን ሁሉ መጽሀፍ ያነባል?
.
እሷ፦ አወ አባየ እንዲት ያለ ስማርት ልጅ መሰለህ!
.
አባት፦በጣም ደስ ይላል እንደዛ ከሆነማ እኔም አንድ መጽሀፍ ልስጥሽና ትወስጅለት አለሽ:
.
እሷ፦ እሽ አባየ የቱን መጽሀፍ ?
.
.
አባት፦ እዛ መደርደሪያ ላይ ሀዲስ አለማየሁ የፃፈው "በናተ ቤት በኮድ አውርታችሁ ልባችሁ ውልቅ ብሏል" የሚለውን!
@semefact
2.6K viewsBķ, 19:55