Get Mystery Box with random crypto!

Rahel Getu - እቴሜቴ Rahel Getu - ነበር @abcdefghijknz እቴሜቴ ሆይ | 𝔪𝔞𝔯𝔨𝔞𝔫 🎼🎵🤪

Rahel Getu - እቴሜቴ
Rahel Getu - ነበር
@abcdefghijknz
እቴሜቴ ሆይ
እቴሜቴ ገላ
መሰለብኝ እንዴ ለፍቅር የማደላ ×፪

ሲባል ነው ወዲያ ማዶ ተከሰተ
ወዲህ መች ይጠፋል ቀልብ የሳተ

ባላይ ባላይ ባላይ ×፬
መልኩ አለ ከአይኔ ላይ

ከሰው ተለይተህ ሳትፈጠር
ምን ይሆን መድመቋ ባንተ ምድር
አትብራ እንደ ኮከብ ....................... አንተ ልጅ
ጊዜው ይጋረዳል ........................... አንተ ልጅ
ቀን እየመሰለው ............................. አንተ ልጅ
ሰው በሌት ይሄዳል ....................... አንተ ልጅ

ቢመስል እንጂ ምኞት መኖር
የታል ውበት አንተ ሳትኖር
ሳይሉት የሰው ቅኔ ዘርፎ
ስንቱ አደረ እሳት አቅፎ

ባላይ ባላይ ባላይ ×፬

እቴሜቴ ሆይ
እቴሜቴ ገላ
መሰለብኝ እንዴ ለፍቅር የማደላ

ከላይ ያለበሰህ ውበት ፈትሎ
ያየህ ሸኘህ አሉ አይኑን ጥሎ

ባላይ ባላይ ባላይ ×፬

እንዲህ ከናፈከኝ ቆመህ ጎኔ
ምን ይውጠኝ ነበር ባትሆን የኔ
አንጀቴ የራሰው .......................... አንተ ልጅ
ሰርክ በመውደዴ ....................... አንተ ልጅ
ውሀ ልቅዳ ብዬ ......................... አንተ ልጅ
አልወርድም እንግዴ ................. አንተ ልጅ

ቢመስል እንጂ ምኞት መኖር
የታል ውበት አንተ ሳትኖር
ሳይሉት የሰው ቅኔ ዘርፎ
ስንቱ አደረ እሳት አቅፎ

ባላይ ባላይ ባላይ ×፬

እቴሜቴ ሆይ
እቴሜቴ ገላ
መሰለብኝ እንዴ ለፍቅር የማደላ................

@abcdefghijknz
@abcdefghijknz