🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

Merega Tv = Ethio 360Media

Logo of telegram channel adawdaa — Merega Tv = Ethio 360Media M
Logo of telegram channel adawdaa — Merega Tv = Ethio 360Media
Channel address: @adawdaa
Categories: News
Language: English
Subscribers: 7.60K
Description from channel

This Is Our Bot Touch It @yolerbot
For Some Comments https://t.me/Meregatvgroup

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


The latest Messages 4

2021-09-27 11:57:25 2014 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

2014 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማውጣት እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን የፀጥታ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በየዓመቱ በመስከረም ወር አጋማሽ ቀናቶች ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ የመስቀል በዓል ነው፡፡

በበዓሉ በርካታ የሃገራችን ብሄር ብሄረሰቦችና የውጭ ሃገር ዜጎችም ጭምር የሚታደሙበት በመሆኑ ወቅታዊውን የፀጥታ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማውጣት እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በሠላም እንዲከበር የአ/አበባ ከተማ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአ/አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር አገራችን ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ልዩ ዝግጅነት ከመደረጉም ባሻገር ለፀጥታ ኃይሉ በበጎ ፈቃደኝነት አጋዥ የሆኑ በቅርቡ የተመረቁ ከ27ሺ በላይ ወጣቶች በፀጥታው ሥራ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስቀድሞ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

በዓሉ ከመስቀል አደባባይ ባሻገር በተለያዩ አድባራት በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ስለሚከበር ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት አንፃር ህብረተሰቡ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ባሟላ ሥነ-ሥርዓት ተሳታፊ እንዲሆን ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የበዓሉ ታዳሚዎች በየአካባቢያቸው በዓሉን ሲያከብሩ እና ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጡ የከተማችን ነዋሪዎች እንደወትሮው ሁሉ የፖሊስን መስተንግዶና ትዕዛዝ በማክበር ተባባሪ እንዲሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ለማስቻል በህገ መንግስታችን እውቅና የሌላቸው ባንድራዎች ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ መልዕክቶችንና አርማዎችን በዓሉ በሚከበርባቸው ቦታዎች ላይ ይዞ መገኘት የተከለከለ መሆኑን ገልፆ መላው የፀጥታ ሃይሉ የተከለከሉ ነገሮችን በህግ አግባብ ለመቆጣጠርና ለማስከበር አስፈላጊው መመሪያ መሰጠቱን ፖሊስ አስታውቋል ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ ሪቺት መተኮስ የተከለከለ ከመሆኑም በሻገር ተቀጣጣይና ስለታማ ነገሮችን በዓሉ ወደ ሚከበርባቸው ቦታዎች ይዞ መምጣት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መስከረም 16 የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚያከናውነውን ተግባር በመደገፍ የከተማችን ነዋሪዎች የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመረጃ ስልኮች 011-1 11-01-11 ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 መረጃ መስጠት እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና መሰከረም 16 ቀን 2014ዓ/ም በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁትን መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

በዚህም መሰረትከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባ፤

ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፤

ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤

ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችር ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤

ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን የኋላ በር መግቢያ፤

ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደፉል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት፤

ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የመወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ እና ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ መንገዱ የሚዘጋ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ሲሆን፣ ደመራው የሚደመርበት መስቀል አደባባይ እና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሴፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገዱ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናል፡፡በመሆኑም ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
1.9K viewsADTNY, 08:57
Open / Comment