🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ድሮ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ እጅግ በጣም ተወዳጅ ከሚባሉት የምግብ አይነቶች መካከል የውሻ ሾርባ እና የ | Asgerami

ድሮ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ እጅግ በጣም ተወዳጅ ከሚባሉት የምግብ አይነቶች መካከል የውሻ ሾርባ እና የውሻ ጥብስ ነው፡፡ ከምርጥ ምግብነት አልፎም ተርፎ ለቆዳ ውበት እና ለስንፈተ ወሲብ ችግር ፍቱን መድሀኒት በመሆኑ ተወዳጅነቱን እጥፍ ድርብ አድርጎላቸዋል! ድሮ የውሻ ስጋ መብላት የኮርያውያን ባህል ቢሆንም ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ተወዳጅነቱ እየቀተሰ መቷል።

በተለይ እንደፈረንጆቹ 2000 ዓ.ም ቡኃላ የተወለዱ ልጆች ይሄ ባህል እንዲቀር እና እንደሚፀየፉት እየተናገሩ ሲሆን። ውሾች የሰው ጓደኛ እንጂ ምግብ አደሉም በሚል የተለያዩ ተቋውሞ ሰልፎች እያካሄዱ ሲሆን መንግስት የውሻ ስጋ መሸጥም ሆነ መግዛት እንዲከለክል እየገፉ ነው። ከዚህም የተነሳ በቅርብ ግዜም የቀድሞ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋች ጂሱንግ ፓርክ ለክለቡ ደጋፊዮች ዘረኝነትን ያዘሉ ቃላቶችን ለሱ ካወጡለት ዝማሬ ላይ እንዲያነሱ ጠየቀ!

በቀያይ ሴጣናቱ ደጋፊዮች ተወዳጅ የሆነዉ ደ.ኮሪያዊዉ ፓርክ ከወር በፊት በሞንሊክስ ዩናይትድ ከዎልቭስ ጋር በነበራቸዉ ጨዋታ ለሱ የወጣለትን ዝማሬ ከረጅም አመታት በኋላ በደጋፊዮች ሲዜም ነበር፤

የሚከለውንም ተናግሮ ነበር

"አዉቃለዉ እናንተ በመጥፎ አስባችሁት አይደለም ለዚህም ነዉ ላስረዳችሁ ምፈልገዉ ያ የምትጠቀሙበት ቃል[dog meat]አሁን በኮሪያ እንደዘረኝነት ነዉ ሚቆጠረዉ፤

በኮርያ አሁን ነገሮች ተቀይረዋል፤ እዉነት ነዉ በታሪካችን የዉሻ ስጋ ተመግበናል፤ አሁን ግን ልጆቻችን በጣም የሚጠሉትና የሚፀየፉት ነገር ነዉ፤ ይህ ትዉልድ ተቀይሯል፤ ስለዚህ የዩናይትድ ደጋፊዮችን የምጠይቀዉ "የዉሻ ስጋ" የምትለዉን ቃል እንድታነሱት ነዉ፤ የሀገሬ ህዝቦች ይህ ቃል ምቾት አይሰጣቸዉም ስለዚህም ይህን ቃል መጠቀም ብታቆሙ።"

@asgerami