🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል። የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪ | Asgerami

ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል።

የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት ለመጀመር በሙከራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ይህ ሥርዓትም ቢያንስ ከ1000 በላይ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ እንደሚጀመር ነው የገለጸው።

ከዚህ ቀደም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት የሌለው ቴሌግራም አሁን ላይ ተጠቃሚዎች ቻናላቸውንና ቡታቸውን በክፍያ እንዲያስተዋውቁ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን ነው ይፋ ያደረገው።

የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ እንደጠቀሰው በሙከራ ላይ የሚገኘው የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓቱ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን የግል መረጃን አይጠቀምም ብሏል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማስታወቂያዎቹ በግል እና በቡድን መልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳዎች ላይ የማይታዩ መሆናቸውንና በክፍያ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች በቻናሎች ላይ ብቻ እንደሚቀርቡ ገልጿል።

ማስታወቂያ ማስነገር የሚፈልጉ አስተዋዋቂዎች ቻናላቸውን ወይም ቡታቸውን ከ160 ባልበለጡ ፊደላት ገለጻ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቋንቋ፣ በይዘት እንዲሁም በልዩነት ማስታወቂያው እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉትን ቻናል መርጠው ማስተዋወቅ ይችላሉ ተብሏል።

ቴሌግራም ከቻናል ባለቤቶች ጋር የትርፍ ክፍፍል የማድረግ እቅድ እንዳለውም ያስታወቀ ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን መሰረታዊ ወጪዎቹን ከሸፈነ በኋላ እንደሆነ ገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot