🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

' ለ11 ቀናት መሳቅ አይቻልም ፤ ወደ መጠጥ ቤት መሄድ እና መጠጥ መጠጣትም አይቻልም ' - ሰሜ | Asgerami

" ለ11 ቀናት መሳቅ አይቻልም ፤ ወደ መጠጥ ቤት መሄድ እና መጠጥ መጠጣትም አይቻልም " - ሰሜን ኮሪያ

የቀድሞውን የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኢልን 10ኛ የሙት ዓመት በማስመልከት በሀገሪቱ ለ11 ቀናት መሳቅ ተከለከለ፡፡

ኪም ጆንግ ኢል ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በአውሮፓውያኑ 2011 ሲሆን ዘንድሮ 10 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡

የቀድሞውን መሪ 10ኛ የሙት ዓመት አስመልክቶም በሀገሪቱ መሳቅና መጠጥ መጠጣት መከልከሉን ዴይሊ ሜል ዘግቧል፡፡

ከዛሬ ጀምሮ ሰሜን ኮሪያውያን ወደ ግሮሰሪ መሄድ እንደማይችሉ የተነገራቸውም ሲሆን በመታሰቢያ የዚህ የሀዘን ቀናቱ ውስጥ ቤተሰቡ የሞተበት ሰው ጮክ ብሎ ማልቀስ እንደማይችል ሰሜን ኮሪያ አስጠንቅቃለች፡፡

የልደት በዓላቸው በ11ዱ የሀዘን ቀናት ውስጥ የሆነባቸው ግለሰቦች ይህንን ማድረግ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።

ዛሬ አርብ ከደቂቃዎች በፊት በፒዮንግያንግ የነበረው የቢዝነስና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ለ5 ያል ደቂቃዎች ቆሞ የኢል 10ኛ ሙት ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በ69 ዓመታቸው በፈረንጆቹ ታህሳስ 17 ቀን 2011 በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ መሪ ሀገራቸውን ለ17 ዓመታት መርተዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ / ዴይሊ ሜይል

@tikvahethiopia