🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ለአዕምሮአችን መቀላጠፍ ና ጤንነት 1. አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው ። በቫይረስ መጠቃት የለበትም | Asgerami

ለአዕምሮአችን መቀላጠፍ ና ጤንነት

1. አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው ። በቫይረስ መጠቃት የለበትም ። ሁልጊዜ ሊጸዳ ይገባዋል፡፡ አእምሮ ከተወዛገበ ሌሎች የሰውነት አካላት መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አእምሮዎ በአስቀያሚ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ማታ ማታ “ስካን” ያድርጉት፡፡ እንዴት ካሉ - በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ለብቻዎ ሆነው ወደ ውስጥ ያሰላስሉ፡፡ በቀን ውስጥ ጥሞና (meditation) ለ30 ደቂቃ ያስፈልጎዋታል፡፡ ደስ የሚሉዎትን ነገር እያሰቡ አእምሮዎን ዘና ያድርጉት፡፡

2. አእምሮ ዕለታዊ ተግባራትን እንዳያከናውን ከሚፈትኑት ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አደገኛ ዕጽ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጫት ነው፡፡ እነዚህ በሙሉ ይነስም ይብዛ አእምሮን ይመርዛሉ፡፡ ማናቸውም አእምሮን ጤናማ ባልሆነ መልኩ የሚያነቃቁ ዕጾች ተግባሩን ያውኩታል ። ያስወግዷቸው፡፡

3. አእምሮ በቀን ውስጥ ምን መስራት እንዳለበት ካልተነገረው ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ በቀን ውስጥ ምን መከወን እንዳለብዎ፣ ምን ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ይንገሩት፡፡ ያንን እንዳሳካ ሲገባው አእምሮ ዘና ይላል፡፡

4. አእምሮዎ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፡፡ ብዙ ሥራ ባሰሩት ቁጥር እየጠነከረ ይመጣል፡፡ አዳዲስ ነገሮችን መማር ይፈልጋል፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች፣ አዳዲስ ፈተናዎች፣ አዳዲስ ጥበቦች እንዲማር እድል ይስጡት፡፡ በዚህ ዘመን 5+9 =14 የሚል ሂሳብ ለመስራት እንኳን ካልኩሌተር ነው የምንጠቀመው፡፡ የቅርብ ጓደኛችንን ስልክ በቃላችን ለመያዝ እንሰንፋለን፡፡ አእምሮ ከሰነፈ ይለግማል፡፡ አእምሯችሁን ቦዘኔ አታድርጉት፡፡ እንዳይዝግባችሁ መጽሐፍ አንብቡለት፡፡


@asgerami