Get Mystery Box with random crypto!

ቱርክ (ተርኪ) ስሟን ወደ ተርኪዬ ቀየረች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በድርጅቱ የቱርክ | Asgerami

ቱርክ (ተርኪ) ስሟን ወደ ተርኪዬ ቀየረች

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በድርጅቱ የቱርክ /ተርኪ ስያሜ ወደ ተርኪዬ መቀየሩን ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

ይህ ተርኪዬ የሚለው ስያሜ የቱርክን ሕዝብ ባህል፣ ሥልጣኔ እና ዕሴቶችን በበለጠ የሚወክል አገላለጽ ነው " በማለት ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ባለፈው ወር ተናግረው ነበር።

ለሀገሪቱ ስያሜ ለውጥ ምክንያት ብሎ ካስቀመጣቸው ነገሮች መካከል " ቱርኪ " የሚለው ስያሜ ምዕራባውያን በዓል ወቅት ለምግብ ከምትቀርበው የዶሮ ዝርያ ጋር መያያዙ እንደሆነ ገልጿል።

በተጨማሪም የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ላይ 'ተርኪ' የሚለው ቃል፤ 'ሙሉ በሙሉ ያልተሳካ' ወይም 'ውድቀት የሆነ ነገር' የሚል ትርጓሜን ይሰጣል።

የቱርክ /ተርኪ መንግስት ሀገሪቱን በአዲስ ስያሜ ተርኪዬ ለማስተዋወቅ ዘመቻ ማድረግ የሰነባበተ ሲሆን በአገሪቱ ተመርተው ወደ ውጪ የሚላኩ ሁሉም ምርቶች ላይ አዲሱ ስያሜ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ካለፈው ጥር ወር ጀምሮም  "ሄሎ ተርኪዬ" የሚል የቱሪዝም ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

መረጃው የ ቲክቫህ ነው።

@asgerami