Get Mystery Box with random crypto!

አጋምና ቁልቋል ባታውቀው ነው እንጂ የውስጤን እውነታ፥የልቤን ቁም ነገር፤ ህመሙ ሳይገባት ከአጋ | ግጥም በድምፅ

አጋምና ቁልቋል

ባታውቀው ነው እንጂ
የውስጤን እውነታ፥የልቤን ቁም ነገር፤
ህመሙ ሳይገባት
ከአጋም የተጠጋ፥ቁልቋል ሆኖ ማደር፤
ስለተለየሁዋት
ሂጅልኝ ስላልኳት
"አትወደኝም" ብላ፥ባልወቀሰች ነበር..!

አጋም እኔነቴን
ከቁልቋል እሷነት፥ላርቀው ስፈልግ፤
"ከዳኸኝ" እያለች
በቃላቷ ሁሉ፥እውንቴን ብትመርግ...
ብ.ት.ሸ.ፋ.ፍ.ነ.ው
በጭንቅላቷ ውስጥ፥ምክንያቴ ቢጣጣል፤
አጠፍከው ብትለኝ
በአንደበትህ ሁሉ፥የገባከውን ቃል፤
አትሞኚ እላለሁ
ስቆ ኖሮ አያውቅም፥ከአጋም ኗሪ ቁልቋል...

እናማ
በንፋስ ሽው ሽው...

ከሾሄ ተጣብቀሽ
ስታለቅሺ እንዳላይ፥ጉዳትሽ ቢከብደኝ፤
የአንቺ ዘለላ እንባ
እንደ ክፉ ቁስል፥እየቆጠቆጠኝ...
ደግሽን በመሻት
ቢቀለኝ ከልብሽ፥ልቤን መነጠሉ፤
ወድጄሽ ብለይሽ
አትበይ "ከድቶኝ ሄደ"፥ ለጠየቀሽ ሁሉ!

                አብርሃም ፍቅሬ
                      (የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1