Get Mystery Box with random crypto!

ሽሽት ''''''' ዝንፈት የለሽም አመለ ቀና፤ ሀሳብሽ ገራም ውልሽ የፀና... ፍፁማዊ  ሰው የህይ | ግጥም በድምፅ

ሽሽት
"''""""
ዝንፈት የለሽም አመለ ቀና፤
ሀሳብሽ ገራም ውልሽ የፀና...
ፍፁማዊ  ሰው
የህይወትሽ ፅዋ ያልተበረዘ፤
የልብሽ መስመር
ውሉን ያላጣ ያልተዛነፈ፤
የአንደበትሽ ቃል
በውሸት መቀስ ያልተቀጠፈ...
የፍፁም እውነት
ፍፁማዊ  ሴት
ፍፁም በፍፁም ቢሆን ያንቺ ጣ'ም፤
እሸሽሽ ጀመር
ቅድስናሽን ፈራሁት በጣም...

ምክንያቱም

ይህ ፍፅምናሽ
የእውነት ከሆነ የሚታይ በሰው፤
ቅድስናሽን እንዳላረክሰው....

ወይም...

ይህ  ፍፅምናሽ
ታይታ ከሆነ ለምድ ያስለበሰሽ፥
ዛሬ ልለይሽ
በማስመሰልሽ ነገ ከምሸሽ...

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1