Get Mystery Box with random crypto!

ስለፍቅር ስትይ አስኪ ለአንዳንድቀን፣ ውዴ አበባ ሁኝ ንብ ሆኜ ልክተምሽ ከሰላለት ገንቦሽ፣ የሚጣ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ስለፍቅር ስትይ

አስኪ ለአንዳንድቀን፣
ውዴ አበባ ሁኝ ንብ ሆኜ ልክተምሽ
ከሰላለት ገንቦሽ፣
የሚጣፍጥ መና ማር ልቀምምልሽ

ሌላ ቀን ላይ ደግሞ፣
በውል የጎመራሽ የፀደይ ወይን ሁኝ
ከማሳው ቀጥፌ፣
አሽቸ ልቃምሽ አንቺን መራብ ይብቃኝ

ሌላም ቀን እንዲሁ፣
ለደረቀ እራሴ የጊደር ቅቤ ሁኝ
ውብ መዓዛሽ ቀልጦ፣
ይስረግ በመንፈሴ ውስጤን ያረስርሰኝ

ደግሞ በአንደኛው ቀን፣
ጸሀይን ሁኝና ልይሽ ሰማዩላይ
የእስትንፋስሽን ፍጅት፣
ቁልቁል ስታስወነጭ ልሙቅ ካለ ከልካይ

አደራ የኔ ውድ፣
አንድ ቀን እንደዛ አንድቀን እንደዚ ስል አትመረሪኝ
ላንቺ ያለኝ ስስት፣
የፍቅርሽ ጥማት ነው ሁሉን የሚያስመኘኝ!

ታደሰ ደምሴ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19