Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ቀልድ ፈገግ****** በላይ በቀለ ወያ . አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እንደ ቀልድ ፈገግ******


በላይ በቀለ ወያ
.
አንቺ እንደምን አለሽ? ፣ እኔን'ኳን አሞኛል
ደህና ነኝ ብልሽም ፣ ሳቄ ይቀድመኛል።
ኑሮ እንዴት ይዞሻል ፣ ባለሽበት ሀገር
እኔ ባለሁበት...
ኢምንት ጉዳይ ነው!
እየሳቁ ውሎ ፣ እየሳቁ ማደር።
ውሸት ነው አትመኝ....
እዚህ ሀዘን የለም ሳቅ ነው የተረፈን
ስላቅ ነው ትርጉሙ...
ሀገር ለቆ ሄዶ፣
"ሀገሬን ሀገሬን" ፣ ብሎ እንደመዝፈን።
............................................
ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? ፣ እኔ አለሁ ታምሜ
ይህን ምፅፍልሽ ፣ ነው ሀኪም ፊት ቆሜ።
ምን አሳቀህ አልሽኝ?
"ምንህን ነው ሚያምህ"...
ብሎ ቢጠይቀኝ
ባኪሙ ጥያቄ ፣ ውስጤ ተገረመ
ምኑን ሀኪም ሆነ...
ማወቅ ከተሳነው ፣ ምኔ እንደታመመ?
...........................................
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ
ልነግርሽ እኮ ነው
ምን ብዬ ልንገርሽ?....
ልነግርሽ ያልሁትን ፣ ሳቄ እያፈነው።
ሃሃሃሃ

እናም እልሻለሁ...
ልነግርሽ ያልሁትን ፣ አልቻልኩም መናገር
ቁም ነገራችንን...
ሳቅ ነው የሚያፍነው ፣ ባለሁበት ሀገር

[ በላይ በቀለ ወያ ]

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19