Get Mystery Box with random crypto!

ሳቅ እንደ መክሊት (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ቁልቋል ደም፤ የነጣው ጥርስሽ ለዛ ተነቅሶ ፥ ለሳቅ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሳቅ እንደ መክሊት
(በእውቀቱ ስዩም)

እንደ ቁልቋል ደም፤ የነጣው ጥርስሽ
ለዛ ተነቅሶ ፥
ለሳቅ ተፈጥረሽ- ጊዜው የለቅሶ ::
ጎጆሽ ግድግዳው ፤ በንባ ቢለሰን
የተጀመረ፤ ደሞ አለው ወሰን::
አዝነን ብንወጥን፤ አዝነን አንቀርም
ይባዛል እንጂ-
ሳቅ እንደ መክሊት አይቀበርም!


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19